መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘካርያስ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን ወደ ላይ ሳነሣ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ሁለቱ ተራሮች የናስ ተራሮች ነበር።
2የመጀመሪያው ሰረገላ ቀይ ፈረሶች ነበሩት፤ ሁለተኛው ሰረገላ ጥቁር ፈረሶች ነበሩት።
3ሦስተኛው ሰረገላ ነጭ ፈረሶች ነበሩት፤ አራተኛው ሰረገላ ዝንጉርጉር ፈረሶች ነበሩት።
4እኔም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት።
5መልአኩም እንዲህ አለኝ’ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ቆመው ከነበሩበት ቦታ የወጡ አራቱ የሰማይ ነፋሶች ናቸው!” አለኝ።
6ጥቁር ፈረሶች ያሉት ወደ ሰሜን፣ ነጭ ፈረሶች ያሉት ወደ ምዕራብ፣ ዝንጉርጉር ፈረሶች ያሉት ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።
7ጠንካሮች ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ፊት ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር፤ ስለዚህም መልአኩ፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ!” አላቸው። እነርሱም ወጥተው ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ።
8ከዚያም ወደ እኔ ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “ወደ ሰሜን እየሄዱ ያሉትን ተመልከት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።”
9የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
10ከምርኮኞቹ ከሔልዳይና፥ ከጦቢያ፣ ከዮዳኤም ወርቅና ብር ወስደህ በዚያው ቀን ከምርኮ ወደ መጣው ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ።
11ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ ኢያሱ ራስ ላይ አድርገው።
12እንዲህም በለው፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እነሆ፣ ስሙ ቁጥቋጥ የተባለው ሰው ይህ ነው! እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የያህዌንም ቤተ መቅደስ ይሠራል!
13የያህዌን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብሩን ይጎናጸፋል፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል። በዙፋኑ ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል።
14ለሔልዳይና፣ ለጦቢያና ለዮዳኤ ክብር አክሊል ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይቀመጣል፤ ለሶፎንያስ ልጅ ቸርነት መታሰቢያ ይሆናል።
15ያኔ በሩቅ ያሉት መጥተው የያህዌን ቤተ መቅደስ ይሠራሉ፤ ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነም ታውቃላችሁ፤ የአምላካችሁን የያህዌን ድምፅ ከልባችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል!”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።