1ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው አንቃኝ።
2እርሱም፣ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም፣ “በዐናቱ ላይ፣ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለመናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ። መቅረዙም ላይ በእያንዳንዱ ጫፍ ሰባት ክሮች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበር።
3ደግሞም አንዱ ከዘይት ማሰሮው በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
4እኔም፣ ያነጋገረኝ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት።
5ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም መልሶ፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።
6ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የመጣው የያህዌ ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ፣ በኀይልና በብርታት አይደለም፤ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
7አንተ ታላቅ ተራራ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች “ሞገስ! ሞገስ ይሁንለት!” ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።
8የያህዌ ቃል ወደ እኔ መጣ፤
9“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት እንደ ጣሉ ሁሉ፣ የእርሱ እጆች ይፈጽሙታል። ያኔ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
10የጥቂቱን ቀን ነገሮች የናቀ ግን ነው? እነዚህ ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። እነዚህ ሰባት መብራቶች በምድር ሁሉ የሚመላለሱ የያህዌ ዐይኖች ናቸው።
11ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ ግራና ቀኝ የቆሙት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” በማለት ጠየቅሁት።
12እንደ ገናም፣ “በሁለት የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅንርንጫፎችስ ምንድን ናቸው?” አልሁት።
13እርሱም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ፤ እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።
14እርሱም፣ “እነዚህ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገለል የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎች ናቸው” አለኝ።