መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘካርያስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ በያህዌ መልአክ ፊት ቆሞ ያህዌ አሳየኝ፤ እርሱን በኃጢአት ልመክሰሰ ሰይጣን በቀኙ በኩል ቆሞ ነበር።
2የያህዌ መልአክ ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን ያህዌ ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ያህዌ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይድለምን?” አለው።
3መልአኩ ፊት ቆሞ በነበረ ጊዜ ኢያሱ ያደፉ ልብሶች ለብሶ ነበር።
4ስለዚህ መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም ኢያሱን፣ “እነሆ፣ ርኩሰትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው።
5መልአኩም፣ “ራሱ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ ያድርጉለት! አለ። እነርሱም የያህዌ መልአክ አጠገቡ ቆሞ እያለ በኢያሱ ራስ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ አደረጉለት፤ ንጹሕ ልብስም አለበሱት።
6በመቀጠል የያህዌ መልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤
7“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ያኔ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ በእነዚህ በፊቴ በቆሙት መካከል እንድትገባና እንድትወጣ አደርግሃለሁ።
8ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ ሆይ ስማ፤ ከአንተ ጋር ያሉት ጓደኞችህም ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፣ ባርያዬን ቁጥቋጡን አመጣለሁ።
9ኢያሱ ፊት ያኖሩትን ድንጋይ ተመልከቱ። በዚያ አንድ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር ኀጢአት በአንድ ቀን አስወግዳለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
10በዚያን ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑና በለስ ዛፉ ሥር እንዲቀመጥ ባልንጀራውን ይጋብዛል” ይላል ያህዌ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።