መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘካርያስ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንደ ገና ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ በእጁ መለኪያገመድ የያዘ ሰው አየሁ።
2እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ፣ “የኢየሩሳሌም ስፋትና ርዝመት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት ነው” አለኝ።
3ከዚያም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ።
4ሁለተኛው መልአክ፣ ሩጥና ለዚያ ወጣት እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ‘በውስጧ ካለው ሕዝብና እንስሶች ባት የተነሣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች።
5ምክንያቱም እኔ ራሴ፣ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር በመካከልዋም ክብር እሆናለሁ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
6ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር አምልጡ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሶች በትኛችኋለሁ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
7እናንት ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሩ፣ ወደ ጽዮን አምልጡ!”
8የሰራዊት ጌታ ያህዌ ካከበረኝና በዘረፉአችሁ ሕዝቦች ላይ ከላከኝ በኋላ፣ እናንተን የሚነካ የእግዚአብሔርን ዐይን ይነካል! ያህዌ ይህን ካደረገ በኋላ፣
9“እኔ ራሴ እጄን በእነርሱ ላይ አንሣለሁ፤ ባርያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል” ያኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
10እኔ ራሴ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና የጽዮን ልጅ ሆይ በደስታ ዘምሪ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
11ከዚያም ቀን ብዙ ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ፤ በመካከልሽ እኖራለሁ” እናንተም ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
12ያህዌም በተቀደሰች ምድር ይሁዳን ርስቱ ያደርገዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ለራሱ ይመርጣታል።
13ከተቀደሰ ማደሪያው ተነሥቷልና፤ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በያህዌ ፊት ጸጥ በል!
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።