1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ የሚል የያህዌ ቃል መጣ፤
2“ያህዌ በአባቶቻችሁ እጅግ ተቆጥቶ ነበር!
3ለሕዝቡ ተናገር፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ወደ እኔ ተመለሱ! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
4“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ!” በማለት በቀድሞ ዘመን ነቢያት እንደ ሰበኩላቸው አባቶቻችሁ አትሁኑ። እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
5ለመሆኑ፣ አባቶቻችሁ ወዴት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?
6ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? እነርሱም ንስሐ በመግባት እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ በወሰነው መሠረት ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።
7ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በመባለው በአሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን ያይህዌ ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ መጣ።
8እነሆም በሌሊት ራእይ አየሁ፤ አንድ ሰው ቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በሸለቆው ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡናማና ነጭ ፈረሶች ቆመው ነበር።
9እኔም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ፣ ምን እንደ ሆኑ፣ አሳይሃለሁ” አለኝ።
10ዛፎች መካከል ቆሞየነበረውም ሰው “እነዚህ በምድር ሁሉእንዲመላለሱ ያህዌ የላካቸው ናቸው”በማለት መለሰ።
11ከዚያም፣ በባርሰነትዛፎች መካከል ቆሞ ለነበረው የያህዌመልአክ፣ “በምድር ሁሉ ተመላለስን፤እነሆ መላዋ ምድር አርፋ ተቀምጣለች”አሉት።
12ያኔ የያህዌ መልአክ መልሶ፣ “የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በእነዚህ ሰባ ዓመቶች ውስጥ የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳላምንና የይሁዳን ከተሞች የማትራራላቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።
13ያህዌም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረው መልአክ ደስ በሚያሰኝ የሚያጽናና ቃል መለሰለት።
14ስለዚህ፣ ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “እንዲህ ብለህ ተናገር፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ!
15ተደላድለውና ተመቻችተው በተቀመጡ ሕዝቦች ላይ በጣም ተቆጥቻለሁ። እኔ የተቆጣሁት በመጠኑ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን ጥፋት እንዲባባስ አድርገዋል።
16ስለዚህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በምሕረቴ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሻለሁ። በውስጧ ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
17ደግሞም፣ እንዲህ በማለት ተናገር፣ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ከተሞቼ እንደ ገና በመልካም ነገሮች ይሞላሉ፤ ያህዌ እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ እንደ ገና ኢየሩሳሌምን ይመርጣታል።
18ከዚያ ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ አራት ቀንዶች ተመለከትሁ!
19ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረውም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።
20ከዚያም ያህዌ አራት የእጅ ባለ ሙያዎች አሳየኝ።
21እኔም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ አራት ቀንዶች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች የመጡት ግን እነርሱን ለማስወጣትና ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን ሕዝቦች ቀንዶች ሰባብሮ ለመጣል ነው” በማለት መለሰልኝ።