1በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን ኀጢአትና ርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
2በዚያ ቀን ከእንግዲህ አስታዋሽ እንዳይኖራቸው የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ አጠፋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። ሐሰተኛ ነቢያትንና ርኵሳን መናፍስቶቻቸውም ከምድሪቱ ይወገዳሉ።
3ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባት እናቱ፣ “በያህዌ ስም ሐሰት ተናግረሃልና ትሞታለህ!” ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።
4በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው ትንቢት ራእይ ያፍራል። እነዚህ ነቢያት ሕዝቡን ለማታለል ከእንግዲህ ጠጕራም ልብስ አይለብስም።
5እያንዳንዱ፣ “እኔ ገበሬ እንጂ፣ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ኑርዬ የተመሠረተውም በዚሁ ነበር!” ይላል።
6ሌላውም መልሶ፣ “ታዲያ፣ ክንዶችህ” መካከል ያሉት እነዚህ ቁስሎች ምንድናቸው?” በማለት ቢጠይቀው፣ “በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ ያቆሰልሁት ነው” በማለት ይመልሳል።
7“ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛ፣ ለእኔ ቅርብ በሆነው ላይ ተነሣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እረኛውን ምታው በጎቹም ይበተናሉ! እኔም ክንዴን በታናናሾች ላይ አዘራለሁ።
8የምድሩ ሁሉ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል! ሰዎች ይሞታሉ አንድ ሦስተኛው ብቻ ይተርፋል ያላል ያህዌ።
9እንደ ብር እንደነጹ፣ ያንን አንድ ሦስተኛ ሕዝብ በእሳት ውስጥ አሳልፋለሁ፤ ወርቅ እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ። ስሜን ይጠራሉ፣ እኔም እመልስላቸዋለሁ ‘ይህ ሕዝቤ ነው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ “ያህዌ አምላኬ ነው!” ያላሉ።