1ስለ እስራኤል የተነገረው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ፣ የሰውን መንፈስ የሠራ ያህዌ እንዲህ ይላል፣
2“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የሚያንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ። ኢየሩሳሌም በምትከበብበት ጊዜ ይሁዳም ላይ እንደዚያው ይሆናል።
3በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን አሕዛብ ሁሉ ላይ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ። ያንን ድንጋይ ማንቀሳቀስ የሚሞክር ሁሉ ክፉኛ ይጎዳል፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዚያች ከተማ ላይ ይሰበሰባሉ።
4በዚያ ቀን፣ ፍረሱን ሁሉ በሽብር፣ የተቀመጠበትንም ሁሉ በእብደት እመታለሁ። የይሁዳን ቤት በምሕረት አያለሁ፤ የጠላትን ፈረስ ሁሉ አሳውራለሁ።
5በዚያ ጊዜ የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ አምላካቸው ስለ ሆነ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርታታችን ናቸው!” ይላሉ።
6በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በእንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ በነዶም መካከል እንዳለ ችቦ ነበልባል አደርጋለሁ፤ በቀኝና በግራ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌምም እንደ ገና ከምድሯ ትኖራልች።
7የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ፣ በዚያ ቀን ያህዌ በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል።
8በዚያ ቀን ያህዌ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከለላ ይሆናል፤ በዚያ ቀን በመካከላቸው ያለው ደካማው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም በፊታቸው እንደ አምላክ፣ እንደ ያህዌም መልአክ ይሆናል።
9በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡ ሕዝቦችን ሁሉ ማጥፋት እጀምራለሁ።
10በዚያ ቀን በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ ወጉኝ ወደ እኔ ይመለክታሉ፤ እነርሱም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ሰው ያለቅሱልኛል፤ ለበኩር ልጁ ሞት እንደሚያለቅስ ሰው ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
11በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚሆነው ለቅስ በመጊዶ ሜዳ ለሐዳድ ሪሞን እንደ ተለቀሰው ታላቅ ለቅሶ ይሆናል።
12ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የእያንዳንዱ ወገን ቤተ ሰብ ለየራሱ ያለቅሳል። የዳዊት ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣
13የሌዊ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰማኢ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣
14የቀሩትም ወገኖች ወንዶች ሁሉ ከነሚስቶቻቸው ያለቅሳሉ።