1እነሆ፣ ብዝበዛሽን በውስጥሽ የሚከፋፈሉበት ቀን ይመጣል።
2ሕዝብን ሁሉ ለጦርነት ኢየሩሳሌም ላይ አስነሣለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች። ቤቶች ይበዘበዛሉ፣ ሴቶች ይነወራሉ። የከተማው ግማሽ ሕዝብ በምርኮ ይወሰዳል፤ የተቀረው ሕዝብ ግን ከከተማው አይጠፋም።
3ነገር ግን በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ ያህዌ እነዚያን ሕዝቦች ይዋጋል።
4በዚያ ጊዜ እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው ደብረ ዘይት ተራራ ይቆማሉ። የደብረ ዘይት ተራራ በመካከሉ ባለው ታላቅ ሸለቆ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ለሁለት ይከፈልና እኩሌታው ወደ ሰሜን፣ እኩሌታው ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።
5እናንተም በያህዌ ተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ በኩል ታመልጣላችሁ፤ በእነዚህ ተራሮች መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳል። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ። ያኔ አምላኬ ያህዌ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ቅዱሳኑ ይመጣሉ።
6በዚያ ቀን ብርሃን አይኖርም፣ ብርድና ውርጭም አይኖርም።
7በዚያ በእግዚአብሔር ብቻ በሚታወቅ ቀን ቀንም ሆነ ማታ ከኢየሩሳሌም ይፈስሳል።
8ክረምትም ሆነ በጋ እኩሌታው ወደ ምሥራቅ ባሕር፣ እኩሌታው ወደ ምዕራብ ባሕር ይፈስሳል።
9ያህዌ በመላው ምድር ይነግሣል። በዚያ ቀን አንድ አምላክ ያህዌ ብቻ ይሆናል፤ ስሙም አንድ ይሆናል።
10ከጌባ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሬሞን ድረስ ምድር ሁሉ እንደ አረባ ትሆናለች። ኢየሩሳሌም ከፍ እንዳለች ትዘልቃለች። ከብንያም በር አንሥቶ የመጀመሪያው በር እስከ ነበረበት እስከ ማእዘኑ በር ድረስ፣ ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ ወይን መርገጫ ድረስ በቦታዋ ትኖራለች።
11ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ይኖራል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ ጥፋት አይመጣባቸውም፤ ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች።
12ኢየሩሳሌምን በወጉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያህዌ የሚያመጣባቸው መቅሠፍቶች እነዚህ ናቸው፤ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል። ዐይኖቻቸው ጉድጓዶቻቸው ውስጥ እያሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸው አፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
13በዚያ ቀን ከያህዌ ዘንድ ታላቅ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱ ሌላውን ይወጋል።
14ይሁዳም ኢየሩሳሌምን ይወጋል። የአካባቢውን ሕዝቦች ሁሉ ሀብት ይሰበስባሉ፤ ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይኖራል።
15ፈረሶችና በቅሎዎች ላይ፣ ግመሎችና አይሆች ላይ መቅሠፍት ይወርዳል፤ ይኸው መቅሠፍት በየሰፈሩ ያሉ እንስሳትንም ሁሉ ይመታል።
16ኢየሩሳሌምን ከወጓት ሕዝቦች ከሞት የተረፉት ለንጉሡ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።
17በምድር ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጣ ካለ፣ ያህዌ ደግሞ ዝናብ አያዘንብላቸውም።
18የግብፅ ሕዝብ የማይወጣ ከሆነ ዝናብ አያገኝም። የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጡ ሕዝቦች ላይ መቅሠፍት ከያህዌ ዘንድ ይመጣባቸዋል።
19የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጣው ግብፅና ማንኛውም ሕዝብ ላይ የሚመጣው ቅጣት ይህ ይሆናል።
20በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፣ “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ይቀረጻል፤ በእግዚአብሔር ቤት ያሉት መታጠቢያዎች መሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች የተቀደሱ ይሆናሉ፤
21በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉት ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ይቀደሳሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ በእነርሱ በማብሰል ይበሉባቸዋል። በዚያ ቀን በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት ውስጥ ከእንግዲህ ነጋዴዎች አይኖሩም።