መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘካርያስ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት ዝግባሽን እንዲበላው በሮችሽን ክፈቺ!
2የጥድ ዛፍ ሆይ፣ ዝግባ ውድቋልና አልቅስ! ግርማ የነበራቸው ዛፎች ጠፍተዋል! ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯልና እናንት የባሳን ወርካዎች ሆይ አልቅሱ።
3ክብራቸው ጠፍቷልና እረኞች ሆይ ጩኹ!
4አምላኬ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “ለእርስ የተለዩትን በጎች እንደ እረኛ አሰማራ!
5የሚገዟቸው ያርዷቸዋል ሳይቀጡም ይቀራሉ፤ የሚሸጧቸውም፣ “ሀብታም ሆኛለሁና ያህዌ ይመስገን” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳ አይራሩላቸውም።
6ከእንግዲህ እኔም በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራም! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ ራሴ ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ። ይሁዳንም ከእጃቸው አልታደገውም።”
7ስለዚህ እኔ ለእርድ ለተለዩትና ለተጨቆኑት እረኛ ሆንሁ። ሁለት በትሮች ወስጄ እንዱን፣ “ሞገስ” ሌላውንም፣ “አንድነት” ብዬ ጠራኋቸው። መንጋውንም አሰማራሁ።
8በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ፤ ትዕግሥቴ አለቀ፤ እነርሱም እንዲሁ እኔን ጠሉኝ።
9ከዚያም ለበጎቹ ባለቤቶች፣ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱ በጎች ይሙቱ፤ የሚጠፉት በጎች ይጥፉ። የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።
10ከዚያም፣ ከነገዶቼ ሁሉ ጋር ያደረግሁት ኪዳን መቋረጡን ለማመልከት፣ “ሞገስ” የተባለው በትሬን ሰበርሁ።
11በዚያ ቀን ኪዳኑ ፈረስ፣ ብጎቹን ያስጨነቁትና ሲመለከቱኝ የነበሩትም ያህዌ እንደ ተናገረ አወቁ።
12እኔም፣ “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደመወዜን ክፈሉኝ፤ ካልመሰላችሁም ተዉት” አልኋቸው። ስለዚህ ሰላሣ ብር ከፈሉኝ።
13ያህዌም፣ “ሊከፍሉህ የተስማሙትን ጥሩ ዋጋ ሰላሣ ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ አኑረው” አለኝ። ስለዚህም ሰላሣውን ብር ወስጄ በሃህዌ ቤት ባለው ግምጃ ቤት ውስጥ አኖሩሁት።
14ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መፍረሱን ለማመልከት፣ “አንድነት” የተባለው ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።
15ያህዌም እንዲህ አለኝ፤ “እንደ ገና የሰነፍ እረኛ ዕቃ ውሰድ፣
16እነሆ እኔ በምድሪቱ ላይ እረኛ ላስነሣ ነው። እርሱም ለጠፋው በግ አያስብም፤ የባዘነውን በግ አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ ጤነኛውን አይመግብም፤ ሆኖም፣ የሰባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኮናው እንኳ ሳይቀር ይቀለጣጥማል።
17መንጋውን ለሚተው እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ይውጋ! ክንዱ ፈጽማ ትሰልል፤ ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር!”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።