1የበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ጠይቁ፣ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ ያህዌ ነው እርሱ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም ይሰጣል።
2የቤተ ሰብ ጣዖቶች ውሸት ይናገራሉ፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ አሳሳች ሕልም ይናገራሉ፤ ባዶ መጽናኛ ይሰጣሉ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ይባዝናሉ፣ እረኛ በማጣጥም ይጨነቃሉ።
3ጽኑ ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤ መሪዎችንም እቀጣለሁ። የሰራዊት ጌታ ያህዌ ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃል፤ በጦርነት ጊዜ እንደ ኩሩ የጦር ፈረሱ ያደርጋቸዋል!
4ከይሁዳ ሕዝብ የማእዘን ድንጋይ ይወጣል፤ ከእነርሱ የድንኳን ካስማ ይገኛል፤ ከእነርሱ የጦር ቀስት ይመጣል፤ ከእነርሱ ገዥ ሁሉ ይወጣል።
5በጦርነት ጊዜ ጠላቶቹን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንደሚረግጥ ሰራዊት ይሆናሉ፤ ያህዌ ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ተዋግተው የጦር ፈረሰኞችን ያሸንፋሉ።
6የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ እምራቸዋለሁ፤ ወደ ቦታቸውም እመልሳቸዋለሁ። ከዚህ በፊት በፍጹም ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው ያህዌ ነኝ፤ ጸሎታቸውንም እሰማለሁ።
7በዚያ ጊዜ ኤፍሬም እንደ ብርቱ ጦረኛ ይሆናል፤ ወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ልባቸውን ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ሐሤት ያደርጋሉ። ልባቸው በእኔ ሐሤት ያደርጋል!
8በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፤ በእርግጥ እታደጋቸዋለሁ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን ይበዛሉ!
9በሕዝቦች መካከል ብበትናቸው እንኳ፣ በሚኖሩባቸው ሩቅ አገሮች ሆነው ያስታውሱኛል፤ እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው ይመለሳሉ።
10ከግብፅ ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋልሁ። ቦታ እስኪጠባቸው ድረስ በገልዓድና በሊባኖስ አሰፍራቸዋለሁ።
11በመከራቸው ባሕር ውስጥ አልፋለሁ፤ ምክንያቱም የባሕሩን ማዕበል እመታለሁ፤ የዐባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ግርማ ይወገዳል፤ የግብፅ በትረ መንግሥት ከግብፃውያን ይወገዳል።
12በእኔ በራሴ አበረታቸዋለሁ፤ በስሜ ይመላለሳሉ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።