መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቲቶ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አንተ ግን፣ ከጤናማው ትምህርት ጋር የሚስማማውን ተናገር።
2በእድሜ የገፋ ሰዎች ልከኞች፣ ጨዋዎች፣ ጠንቃቆች ጤናማ እምነት፣ ፍቅርና ጽናት ያላቸው ሊሆኑ ይገባችዋል፡፡
3በእድሜ የገፉ ሴቶችም እንዲሁ ጨዋዎችና፣ ከሃሜት የራቁ መሆን አለባቸው፡፡ ወይን ጠጅ ጠጪዎች መሆን አይገባቸውም። መልካም የሆነውን ማስተማር ይገባችዋል
4ወጣት ሴቶችን በአስተሳሰባቸው ሚዛናዊ እንዲሆኑ እንዲያሳስቧቸው፣ የገዛ ባሎቻቸውና ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እንዲያበርቷቷቸው፣
5የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ንፁህ፣ መልካም የቤት አስተዳዳሪና፣ ለባሎቻቸውም የሚታዘዙ ይሁኑ።
6በተመሳሳይ መንገድ፣ ወጣት ወንዶች ጠንቃቆች እንዲሆኑ አሳስባቸው።
7በነገር ሁሉ ራስህን የመልካም ሥራ ምሳሌ አድርገህ ተገኝ፤ በትምህርትም ንጽህናን፣ ጨዋነት፣ የማይነቀፍ ጤናማ ቃላት ይኑርህ።
8ስለ እኛ የሚናገረው ምንም ክፉ ነገር እንዳይኖር። የማይነቀፍ ስህተት የሌለበትን፣ ነገር ግን ሊቃወም የሚሞክረውን የሚያሳፍር ቃላትን ተናገር።
9ባሪያዎች በሁሉም ነገር ለጌቶቻቸው ይታዘዙ። ጌቶቻቸውን ደስ ሊያሰኟቸው ይሞክሩ እንጂ፣ አይከራከሯቸው።
10ስለ መድሃኒታችን እግዚአብሔር የምናስተምረው፣ በሁሉ መንገድ የሚማርክ እንዲሆን፣ ታማኝነትን ያሳዩ እንጂ አይስረቁ።
11ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡
12ይህም ፀጋ ሃጢዓተኝነትና ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድና፣ በአሁኑ ዘመን በጥንቃቄ፣ በጽድቅና፣ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር ያስለምደናል
13ይህም የተባረከውን ተስፋችንን፣ የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ፣ ለመቀበል በደስታ እንድንጠባበቅ ነው።
14ኢየሱስ ራሱን ለእኛ የሰጠው፣ ከዓመፅ ነፃ ሊያወጣንና ሊያነፃን፣ ገንዘቡና መልካምን ለማድረግ የሚናፍቅ ሕዝብ፣ ለራሱ ሊያደርገን፣ ዋጋ ለመክፈል ነው።
15እነዚህን ነገሮች ተናገር፣ አበረታታ፣ በሙሉ ስልጣን ገስጽ፣ ማንም አይናቅህ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።