መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቲቶ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእግዚአብሔር ባሪያና፣የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፣ በእግዚአብሔር የተመረጡት ሰዎች እምነት እንዲጸና፣ እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማውን የእውነት እውቀት ለማፅናት፣
2የማይዋሽ እግዚአብሔር፣ በተረጋገጠ ዘላለማዊ ሕይወት ከዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ፣
3እንደ መድሃኒታችን እግዚአብሔር ትዕዛዝ፣ በትክክለኛው ጊዜ፣ ቃሉን ለእኔ አደራ በሰጠኝ መልዕክት ገለጠ፡፡
4የጋራችን በሆነ እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለቲቶ። ከእግዚአብሔር አብ፣ከመድሃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋ፣ምህረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።
5አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት፣ ያልተጠናቀቁትን ነገሮች እንድታስተካክልና፣ በነገርኩህ መሠረት በየከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፡፡
6የቤተክርስቲያን ሽማግሌ፣ ነቀፋ የሌለበት፣የአንዲት ሚስት ባል፣ ከክፍዎችና ካልታረሙ ጋር ስማቸው የማይነሳ ታማኝ ልጆች ያሉት ሊሆኑ ይገባዋል።
7የቤተክርስቲያን ሽማግሌ የእግዚአብሔርን ቤት የሚያስተዳድር መሪ ስለሆነ ነቀፋ የሌለበት፣ የማይጮህ፣ራሱን የሚገዛ ፣የማይቆጣ ፣ለወይን ጠጅ የማይገዛ፣ የማይጣላና ስስታም ያልሆነ ሊሆን ይገባል።
8ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፣ መልካምን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ጻድቅ፣ መንፈሳዊና ራሱን የሚገዛ መሆን አለበት።
9በጤናማ ትምህርት ሌሎችን ለማበረታታት፣ የሚቃወሙትን ለመገሠጽ እንዲችል እውነተኛውን ትምህር አጥብቆ መያዝ ይኖርበታል።
10ሥርዓት የሌላቸው በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙዎች አሉ። ቃላቸው ከንቱ ነው። ሰዎችን ያስታሉ፣ በተሳሳተ መንገድም ይመራሉ።
11እነዚህን ዝም ማሰኘት ይገባል። ለነውረኛ ትርፍ ብለው ማስተማር የማይገባቸውን እያስተማሩ፣ መላ ቤተሰብን ያፈርሳሉ።
12ከነሱ ከራሳቸው ነብያት መካከል አንዱ፣ "የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፣ ክፉና አደገኛ አውሬዎች፣ ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው" ብሏል፡፡
13ይህም አባባል ትክክል ነው፣ ስለዚህ ጤነኛ እምነት እንዲኖራቸው አጥብቀህ ገሥጻቸው ።
14ጊዜያቸውን በአይሁድ ተረትና፣ ከእውነት በራቁ ሰዎች ትዕዛዛት ላይ አያባክኑ።
15ንጹሆች ለሆኑት፣ ሁሉም ንጹህ ነው፣ ለርኩሶችና ለማያምኑ ግን ንጹህ የሆነ ምንም የለም። ይልቁን፣ አዕምሯቸውና ሃሳባቸው እንኳ የረከሰ ነው፡፡
16እግዚአብሔር እንደሚውያቁ ይናገራሉ፣ በሥራቸው ግን ይክዱታል። የሚያስጸይፉ የማይታዘዙና፣ ለመልካም ስራም የማይበቁ ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።