መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ቲቶ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች እንዲገዙ፣ እንደታዘዟቸው፣ ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ እንዲሆኑ፣
2ማንንም እንዳይሳደቡ፣ የሌሎችንም ፈቃድ እንዲያከብሩ እንጂ እንዳይከራከሩ፣ ለሁሉም ሰው ትህትን እንዲያሳዩ አሳስባቸው።
3እኛም ቀድሞ የማናስተውልና የማንታዘዝ ነበርን። የሳትንና የተለያዩ ምኞቶቻችንና ፍላጐቶቻችን ባሪያዎች ነበርን። በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር። የተጠላንና እርስበርስ የምንጠላላ ነበርን።
4ነገር ግን፣ የመድሃኒታችን የእግዚአብሔር ርህራሔና ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣
5ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።
6እግዚአብሔር በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፣ አብዝቶ መንፈስ ቅዱስን አፈሰሰልን።
7ይህም በፀጋው ፀደቅን፣ የዘላለም ህይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን ነው።
8እነዚህ ቃሎች የታመኑ ናቸው። በእግዚአብሔር የሚያምኑ እርሱ በፊታቸው ላኖረው መልካም ሥራ እንዲተጉ፣ እነዚህን ነገሮች በድፍረትት እንድትናገር እፈልጋለሁ። እነዚህ ነገሮች መልካምና ለሰዎች ሁሉ የሚጥቅሙ ናቸው።
9ነገር ግን ከከንቱ ክርክር፣ ከዘር ቆጠራና በህግ ጉዳይ ከሚሆን ጸብና ግጭት ራቅ። እነዚህ ነገሮች፣ የማይገቡና የማይጠቅሙ ናቸው፡፡
10አንዴ ወይም ሁለቴ ካስጠነቀቅከው በኋላ፥ በመካከሃላችሁ መከፋፈል የሚፈጥረውን ሰው አስወግደው፡፡
11እንዲህ ዓይነቱ ሰው፣ ከእውነተኛው መንገድ የወጣ፣ ሃጢያት የሚያደርግና በራሱ የፈረደ እንደሆነ እወቅ።
12አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፣ ክረምቱን ለማሳለፍ ወደ ወሰንኩበት ወደ ኒቆሊዎን ፈጥነህ ና።
13የህግ ባለሞያውን፣ ዜማስንና አጵሎስን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሰጥተህ ቶሎ ላካቸው።
14ወገኖቻችንም እለታዊ ፍላጎታቸውን ማግኛት እንዲችሉ ፍሬ ቢስም ሆነው እንዳይገኙ፣ መልካም ሥራ ማድረግን መማር አለባቸው።
15ከኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል ። የሚወዱንን አማኞችን ሁሉ ሰላም በልልን። ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።