1አንቺ የልዑል ልጅ! እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ? የዳሌዎችሽ ቅርጽ በእውቅ አንጥረኛ እጅ የተሠሩ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።
2እንብርትሽ ክብ ጽዋ ይመስላል፤ ድብልቅ ወይን በፍጹም አይጉደለው። ሆድሽ በአበቦች የተከበበ የስንዴ ክምር ይመስላል።
3ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የሜዳ ፍየሎችን፥ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን ይመስላሉ።
4አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ የጥበቃ ማማ ይመስላል፤ ዓይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ በሐሴቦን ያሉትን ኩሬዎች ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ የሚመለከተውን በሊባኖስ ያለውን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
5ራስሽ በአንቺ ላይ የቀርሜሎስን ተራራ ይመስላል፤ በራስሽ ላይ ያለው ጸጉር ጥቁር ሐምራዊ ነው። ንጉሡ በረጅሙ ጸጉርሽ ተይዞ ታስሮአል።
6ተወዳጇ ሆይ፥ እንዴት የምታስደስቺ፥ ውብና ያማርሽ ነሽ!
7ቁመትሽ የቴምር ዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም እንደ ተከማቹ ፍሬዎች ናቸው።
8እኔም፥ "በዚያ የዘንባባ ዛፍ ላይ እወጣለሁ፤ ቅርንጫፎቹንም እይዛለሁ" ብዬ አሰብኩ። ጡቶችሽ የወይን ክምችቶች ይሁኑ፥ የአፍንጫሽ እስትንፋስ መዓዛውም እንደ እንኮይ ይሁኑ።
9አፍሽ እንደ ምርጥ የወይን ጠጅ ይሁን፥ በዝግታም በውዴ ከንፈርና ጥርስ እየፈሰሱ ይንቆርቆሩ። ወጣቷ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥
10እኔ የውዴ ነኝ፥ እርሱም ይመኘኛል።
11ውዴ ሆይ ና፥ ወደ ገጠር እንሂድ፥ በመንደሮቹም እንደር።
12ወደ ወይኑ ቦታ ለመሄድ ማልደን እንነሣ፤ ወይናቸው አፍርቶ፥ አበባቸውም ፈክቶ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ እንይ። በዚያም ፍቅሬን እሰጥሃለሁ።
13ትርንጉዎች መዓዛቸውን ሰጡ፤ በምንቆይበት ቤት ደጃፍ ሁሉም ዓይነት የተመረጡ ፍሬዎች አሉ፥ አዲስና የቆዩ፥ ውዴ ሆይ፥ ለአንተ አስቀምጫቸዋለሁ።