መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እህቴ፥ ሙሽራዬ፥ ወደ አትክልቴ ቦታ መጣሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ። የማር እንጀራዬን ከወለላው ጋር በልቻለሁ፤ ወይኔን ከወተቴ ጋር ጠጥቻለሁ። ጓደኞች ለአፍቃሪዎች ሲናገሩ፥ ጓደኞቻችን ሆይ ብሉ፤ ጠጡ፥ በፍቅርም ስከሩ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥
2እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን በሕልም ነቅቷል። የውዴ ድምጽ ነው፥ በሩን ያንኳኳል፥ "እህቴ፥ ውዴ፥ እርግቤ፥ እንከን የሌለብሽ ሆይ፥ ራሴ በጤዛ ርሷል ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት፥ ስለዚህ ክፈችልኝ" እያለ።
3"ልብሴን አውልቄአለሁ፤ እንደገና መልበስ አለብኝ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ ማቆሸሽ አለብኝ?"
4ውዴ በበሩ መካፈቻ ቀዳዳ በኩል እጁን አስገባ፥ ልቤም ስለ እርሱ ታወከ።
5ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፥ እጆቼ ከርቤን አንጠባጠቡ፥ ጣቶቼ በበሩ እጀታ ላይ በከርቤ ረጠቡ።
6ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፥ ውዴ ግን ተመልሶ ሄዶ ነበር። ልቤ ደነገጠ፤ እኔም ተከፋሁ። ፈለግሁት፥ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
7ጠባቂዎቹ በከተማ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ጠባቂዎችም ካባዬን ወሰዱብኝ። ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥
8እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ ውዴን ካገኛችሁት ለእርሱ ካለኝ ፍቅር የተነሣ መታመሜን ልትነግሩት ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። የከተማው ሴቶች ለወጣቷ ሲናገሩ፥
9አንቺ በሴቶች መካከል የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ ወንድ የተሻለው እንዴት ነው? እንዲህ ያለውን መሐላ እንድናደርግ የጠየቅሽን ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ የተሻለው ለምንድነው? ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥
10ውዴ ደስተኛና ቀይ ነው፥ ከአሥር ሺዎችም የላቀ ነው።
11ራሱ ንጹህ ወርቅ ነው፤ ፀጉሩም ዞማና እንደ ቁራ የጠቆረ ነው።
12ዓይኖቹ በጅረት አጠገብ እንዳሉ እርግቦች፥ በወተት እንደ ታጠቡ፥ በማስቀመጫቸው ያሉ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።
13ጉንጮቹ የሽቶ መዓዛ የሚሰጡ የልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም መደብ ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ከርቤን የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።
14ክንዶቹ የዕንቁ ፈርጥ ባለበት ወርቅ ተሸፍኗል፤ ሆዱ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው።
15እግሮቹ በንጹህ የወርቅ መሠረት ላይ የቆሙ፥ የእምነ በረድ ምሶሶዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ተመረጠም ዝግባ ነው።
16አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ እርሱ ፍጹም ውብ ነው። የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ጓደኛዬም እርሱው ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።