መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኦ፥ ወዳጄ ሆይ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ እነሆም ቆንጆ ነሽ። በመሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እርግቦች ናቸው። ጸጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል።
2ጥርስሽ በቅርቡ ተሸልቶ ከመታጠቢያው ሥፍራ የሚወጣውን የበግ መንጋ ይመስላል። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም።
3ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽ ውብ ነው። ጉንጮችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላል።
4አንገትሽ በረድፍ በተደረደሩ ድንጋዮች ላይ የተገነባውን የዳዊትን የጥበቃ ማማ ይመስላል፥ አንድ ሺህ ጋሻ፥ የወታደሮቹ ሁሉ ጋሻ በእርሱ ላይ ተሰቅሏል።
5ሁለቱ ጡቶችሽ በአበቦች መካከል የተሰማሩ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን፥ መንታም የተወለዱ የሜዳ ፍየሎችን ይመስላሉ።
6ጎሕ እስኪቀድና ጥላው እስኪሸሽ ድረስ፥ ወደ ከርቤው ተራራ፥ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።
7ውዴ ሆይ፥ ሁለመናሽ ውብ ነው፥ እንከንም የለብሽም።
8ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ። አዎን፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፥ ከአማና ጫፍ፥ ከሳኔርና ከኤርሞን ጫፍ፥ ከአንበሶች ዋሻ፥ የነብሮች ዋሻ ከሆነውም ተራራ ነይ።
9እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ ዕይታሽ ብቻ፥ በአንድ ሐብልሽ ብቻ ልቤን ሰርቀሽዋል።
10እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያማረ ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ ይሻላል፥ የሽቶሽ መዓዛም ከቅመሞች ሁሉ።
11ሙሽራዬ ሆይ፥ ከንፈሮችሽ ማር ያንጠባጥባሉ፥ ማርና ወተት ምላስሽ ሥር ናቸው። የልብሶችሽ መዓዛ የሊባኖስን መዓዛ ይመስላል።
12እህቴ ሙሽራዬ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ ናት፥ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ፥ የታተመበትም ምንጭ።
13ቅርንጫፎችሽ የሮማን ዛፍ ከተመረጠ ፍሬ ጋር፥ ሂናና የናርዶስ ተክል፥
14ናርዶስና ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ ከልዩ ልዩ ቅመሞች ጋር፥ ከርቤና እሬት ምርጥ ከሆኑት ቅመሞች ሁሉ ጋር አሉባቸው።
15አንቺ የአትክልት ሥፍራ ምንጭ፥ የንጹህ ውሃ ጉድጓድ፥ ከሊባኖስ ወደ ታች የሚወርድ ምንጭ ነሽ። ወጣቷ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
16የሰሜን ንፋስ ሆይ ንቃ፤ የደቡቡም ንፋስ ና፤ ቅመሞቹ መዓዛቸውን እንዲሰጡ በአትክልት ሥፍራዬ ላይ ንፈስ። ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ ይምጣ፥ ከምርጡም ፍሬ ጥቂት ይብላ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።