1ሌሊት በመኝታዬ የምወደውን ናፈቅሁት፤ ፈለግሁት፥ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም።
2እኔም ለራሴ፥ "እነሣለሁ፥ ወደ ከተማው ውስጥ፥ ወደ ጎዳናዎቹና ወደ አደባባዮቹ እሄዳለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ" አልኩ። ፈለግሁት፥ ላገኘው ግን አልቻልኩም።
3ጠባቂዎች በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ሲዘዋወሩ አገኙኝ። እኔም፥ "ውዴን አይታችሁታል?" ብዬ ጠየቅኋቸው።
4ከእነርሱ ጥቂት እልፍ እንዳልኩኝ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት። ያዝኩት፥ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ፀነሰችኝም መኝታ ቤት እስካመጣው ድረስ አልለቀውም። ሴቲቱ ለሌላይቱ ሴት ስትናገር፥
5እናንተ የኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና አጋዘኖች እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። ወጣቷ ሴት ለራሷ ስትናገር፥
6ይህቺ በዕጣንና ከርቤ፥ ነጋዴዎችም በሚሸጡት ልዩ ልዩ ቅመም በተቀመመ ሽቶ ተቀብታ እንደ ጢስ ምሶሶ ከምድረ በዳ የምትወጣ ማናት?
7እነሆ እርሱ የሰለሞን ተንቀሳቃሽ አልጋ ነው፤ ስልሳ የእስራኤል ወታደሮች፥ ስልሳ ጦረኞች ከብበውታል።
8እነርሱ በሰይፍ የላቁ ናቸው፥ በጦርነትም የታወቁ። እያንዳንዱ በወገቡ ሰይፍ አለው፥ በሌሊት የሚያሸብሩትን ለመከላከል ታጥቀዋል።
9ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ በመጣ እንጨት ሰው ተቀምጦበት የሚሸከሙትን [ለአንድ ሰው መቀመጫ የሚሆን ወንበር የሚይዝ] ሳጥን ለራሱ ሠራ።
10ምሶሶዎቹን ከብር፥ ጀርባው ከወርቅ፥ መቀመጫው ከሐምራዊ ጨርቅ ተደርጎ ተሠራ። ውስጡ የተዋበው በኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች ነበር። ወጣቷ ለኢየሩሳሌም ሴቶች ስትናገር፥
11የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሂዱ ውጡ፥ ንጉሥ ሰለሞንን ትኩር ብላችሁ እዩት፥ በሕይወቱ በተደሰተባት በዚያች ቀን፥ በሠርጉ ቀን እናቱ የደፋችለትን አክሊል ጭኖ።