መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እኔ በሜዳ የሚገኝ አበባ፥ በሸለቆም የሚገኝ አበባ ብቻ ነኝ። ሰውየው ሲናገራት፥
2ውዴ ሆይ፥ አበባ በእሾህ መካከል እንደሆነ አንቺም በሀገሬ ሴቶች ልጆች መካከል ነሽ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
3በዱር ዛፍ መካከል እንዳለ የእንኮይ ዛፍ የእኔም ውድ በጎልማሶች መካከል ነው። በታላቅ ደስታ ከጥላው ሥር ተቀመጥኩ፥ የፍሬውም ጣዕም ጣፋጭ ነው።
4ወደ ግብዣው አዳራሽ አመጣኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ሰንደቁ ፍቅር ነው። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
5በዘቢብ ጥፍጥፍ ነፍስ ዝሩብኝ፥ በእንኮይ ጭማቂም አበርቱኝ፥ በፍቅር ተይዤ ደክሜአለሁና። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
6ግራ እጁ ከአንገቴ ሥር ነው፥ ቀኝ እጁም ያቅፈኛል። ሴቲቱ ለሌላዋ ሴት ስትናገር፥
7የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን ወቅት እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና በአጋዘኖች ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥
8የውዴ ድምጽ ነው! ኦ፥ በተራራዎች ላይ እየዘለለ፥ በኮረብታዎች ላይ እየተስፈነጠረ ሲመጣ ይታወቀኛል።
9ውዴ የሜዳን ፍየል ወይም ግልገል አጋዘንን ይመስላል፤ እነሆ እርሱ ከቤታችን ግድግዳ በስተኋላ ቆሟል፥ በመስኮቱ በኩል አተኩሮ፥ በፍርግርጉም አጮልቆ ይመለከታል።
10ውዴ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ "ውዴ ሆይ ተነሽ፤ የኔዋ ቆንጆ ከእኔ ጋር ነይ።
11ተመልከች፥ ክረምቱ አልፏል፥ ዝናቡም ቆሟል፥ ሄዷልም።
12አበቦች በምድር ላይ ታይተዋል፤ ወይን የሚገረዝበትና የወፎች ዝማሬ ጊዜ ደርሶአል፥ የእርግቦችም ድምጽ በምድራችን ተሰምቷል።
13የበለስ ዛፍ አረንጓዴ ፍሬዎቿ በስለዋል፥ ወይኖቹም አብበዋል፥ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል። ውዴ ሆይ ተነሽ፥ የኔዋ ቆንጆ ነይ።
14በዐለት ሥንጣቂ ውስጥ፥ በድብቁ የተራራማው ቋጢኝ ስንጣቂ ውስጥ ያለሽ እርግቤ ሆይ፥ ፊትሽን ልየው። ድምጽሽን ልስማው፥ ድምጽሽ ጣፋጭ ነውና ፊትሽም ውብ ነው።" ሴቲቱ ለራሷ ስትናገር፥
15የወይናችን ቦታ አብቦአልና የወይን ቦታዎችን የሚያበላሹትን ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን።
16ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ እርሱ መንጋውን በአበቦቹ መካከል በደስታ ያሰማራል።
17ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ውዴ ሆይ፥ ተመለስ፣ የንጋቱ ቀዝቃዛ ንፋስ ሳይነፍስ፥ ጥላውም ሳይሸሽ። ተመለስ፤ በጎርበጥባጣዎቹ ኮረብቶች ላይ የሜዳ ፍየልን ወይም ግልገል አጋዘንን ምሰል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።