መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከመዝሙሮች የሚበልጥ የሰለሞን መዝሙር። ልጃገረዲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥
2ኦ በአፍህ መሳም በሳምከኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይሻላልና።
3ሽቶህ አስደሳች መዓዛ አለው፤ ስምህ እንደሚፈስ ሽቶ ነው፥ ስለዚህ ልጃገረዶች ወደዱህ።
4ካንተ ጋር ውሰደኝ፥ አብረንም እንሮጣለን። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥ ንጉሡ ወደ ቤቱ ውስጥ አስገባኝ። ሴቲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ስትል ትናገረዋለች፥ ደስ ብሎኛል፤ ስለ አንተ ደስ ይለኛል፤ በፍቅርህ ሐሴት ላድርግ፤ እርሱ ከወይን ጠጅ ይሻላል። ሌሎቹ ሴቶች ቢያደንቁህ ተፈጥሮአዊ ነው
5አንደኛዋ ሴት ለሌላይቱ ስትናገር፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ቢሆንም ውብ ነኝ፥ እናንተ ከኢየሩሳሌም ወንዶች የተወለዳችሁ ሴቶች ልጆች፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች ጥቁር፥ እንደ ሰለሞንም መጋረጃዎች ውብ ነኝ።
6ጥቁር ስለ ሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትመልከቱኝ፥ ምክንያቱም ፀሐይ አጥቁሮኛል። የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቆጡኝ፥ የወይን አትክልት ጠባቂም አደረጉኝ፥ የራሴን የወይን ቦታ ግን አልጠበቅሁም። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
7ንገረኝ የምወድህ፥ መንጋህን የምታሰማራው የት ነው? በቀትር ጊዜስ መንጋህን የምታሳርፈው የት ነው? ከባልንጀሮችህ መንጋ ኋላ እንደሚቅበዘበዝ ሰው ለምን እሆናለሁ? ፍቅረኛዋ ሲመልስላት፥
8ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽው ሆይ፥ አታውቂ እንደሆነ፥ የመንጋዬን ኮቴ ተከተይ፥ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
9የኔ ፍቅር፥ በፈርዖን የሰረገላ ፈረሶች መካከል ካለችው ባዝራ ጋር አመሳሰልሁሽ።
10ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፥ አንገትሽም በዕንቁ ሐብል።
11የብር ፈርጥ ያለበት የወርቅ ማጌጫ እሠራልሻለሁ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
12ንጉሥ ማዕዱ ላይ እያለ፥ የናርዶስ ሽቶዬ መዓዛውን ናኘው።
13ውዴ ለእኔ ልክ ሌሊቱን ሙሉ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።
14ውዴ ለእኔ በዓይንጋዲ የወይን ቦታ ውስጥ እንደ ሂና የአበባ ዕቅፍ ነው። ፍቅረኛዋ ሲናገራት፥
15ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ አንቺ ውብ ነሽ፤ እነሆ ያማርሽ ነሽ፤ ዓይኖችሽ እርግቦችን ይመስላሉ። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
16ውዴ ሆይ፥ እነሆ አንተ መልከ መልካም ነህ፥ ያማርክም ነህ። የለመለመው ሣር እንደ አልጋ ያገለግለናል።
17የቤታችን የማዕዘን ተሸካሚ የዝግባ እንጨት፥ የጣሪያችን ማዋቀሪያም የጥድ እንጨት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።