መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1-3እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ውስጥ መኖራችንን እንቀጥልን? እንዲህ አይሁን። ለኃጢአት የሞትን እኛ እንዴት በእርሱ ውስጥ መኖር እንቀጥላለን? ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የተጠመቁ ሁሉ ወደ ከሞቱ ጋር ለመተባበር እንደተጠመቁ አታውቁምን?
4እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።
5ሞቱን በሚመስለው ከእርሱ ጋር ከተባበርን ከትንሣኤው ጋር ደግሞ እንተባበራለን።
6የኃጢአት ሰውነት ይጠፋ ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ ይህንን እናውቃለን። ይህም የሆነው ከዚህ በኋላ ለኃጢአት እንዳንገዛ ነው።
7ከኃጢአት አኳያ ሲታይ የሞተ ሰው መጽደቁ ታውጆለታል።
8ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር አብረን እንደምንኖር ደግሞ እናምናለን።
9ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣና ሞቶ እንዳልቀረ እናውቃለን። ከዚህ በኋላ ሞት አይገዛውም።
10ስለኃጢአት የሞተው ሞት ለዘላለም የሚሠራ የአንድ ጊዜ ሞት ነው። ይሁንና የሚኖረውን ሕይወት ለእግዚአብሔር ይኖራል።
11ልክ እንደዚሁ እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር እንደምትኖሩ መቁጠር ይገባችኋል።
12ስለዚህ ለክፉ ምኞቱ እንድትታዘዙ በሚፈልግ የሚሞት ሥጋችሁ ላይ ኃጢአት እንዲነግሥ አትፍቀዱለት።
13ከሙታን ሕያው እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የአመጻ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። የሰውነት ክፍሎቻችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።
14ኃጢአት እንዲገዛችሁ አትፍቀዱለት። ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።
15እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ባለመሆናችን ኃጢአት መሥራት አለብን? ከቶ እንዲህ አይሁን።
16ትታዘዙት ዘንድ ራሳችሁን እንደ አገልጋይ ለምታቀርቡለት ለእርሱ አገልጋዮች እንደሆናችሁ አታውቁምን? ወደ ሞት የሚመራችሁ የኃጢአት አገልጋዮች ወይም ወደ ጽድቅ የሚመራችሁ የመታዘዝ አገልጋዮች ናችሁ።
17ቀድሞ የኃጢአት አገልጋዮች ነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁ ትምህርት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
18ከኃጢአት ነጻ ተደርጋችኋል፥የጽድቅም አገልጋዮች ሆናችኋል።
19በሥጋችሁ ድካም ምክንያት እንደ ሰው ልማድ እናገራለሁ። ልክ የሰውነታችሁን ክፍሎች ለእርኩሰትና ለክፋት እንደ ባሪያ አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ እንደዚያው አሁን የሰውነት ክፍሎቻችሁ ሊቀደሱ የጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።
20የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ከጽድቅ ውጪ ነበራችሁ።
21አሁን በምታፍሩባቸው በእነዚያ ነገሮች ያን ጊዜ ምን ተጠቀማችሁባቸው? ምክንያቱም የእነዚያ ነገሮች ውጤት ሞት ነው።
22አሁን ግን ከኃጢአት ነጻ ስለተደረጋችሁና ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ስለሆናችሁ ለመቀደስ ፍሬ ታፈራላችሁ። ውጤቱም የዘላለም ሕይወት ነው።
23የኃጢአት ደሞዝ ሞት ሲሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።