መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህ አንተ ሰው፥ አንተው ፈራጁ እነዚያኑ ነገሮች ስለምታደርግ በሌላው በምትፈርድበት ራስህን ትኮንናለህና የምታመካኘው የለህም።
2ነገር ግን እነዚያን ነገሮች በሚያደርጉት ላይ ቁጣው በሚወርድባቸው ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን።
3ነገር ግን አንተው ራስህ ያንኑ እያደረግህ እንደነዚያ ያሉትን በሚያደርጉት ላይ የምትፈርድ አንተ ሰው፥ይህንን አስተውል። ከእግዚአብሔር ፍርድ ታመልጣለህን?
4ወይስ የቸርነቱን ባለጠግነት፥የቅጣቱን መዘግየትና ትዕግስቱን ታቃልላለህን? ቸርነቱ ወደ ንስሐ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?
5ነገር ግን በፍርድ ቀን ያም የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ በሚገለጥበት ጊዜ በድንዳኔህና ንስሐ በማይገባው ልብህ መጠን ለራስህ ቁጣን ታከማቻለህ።
6እርሱ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል፤
7በበጎ ተግባር በመጽናት ምስጋናን፥ክብርንና የማይጠፋውን ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል።
8የራሳቸውን ጥቅም በሚፈልጉት፥ለአመጻ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙት ላይ ግን መቅሰፍትና ብርቱ ቁጣ ይመጣባቸዋል።
9አስቀድሞ በአይሁዳዊ ቀጥሎም በግሪክ ሰው፥ክፋትን ባደረገ ነፍስ ሁሉ ላይ እግዚአብሔር መከራና ጭንቀትን ያመጣባቸዋል።
10አስቀድሞ ለአይሁድ ቀጥሎም ለግሪክ መልካም ላደርጉ ሁሉ ግን ምስጋና፥ክብርና ሰላም ይሆንላቸዋል።
11እግዚአብሔር ስለማያዳላ
12ሕግ እያላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፥ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ደግሞ ያለ ሕግ ይጠፋሉ።
13በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕጉን የሚሰሙት ሳይሆኑ ሕጉን የሚያደርጉት ናቸው።
14ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮአቸው የሕጉን ነገሮች በሚፈጽሙበት ጊዜ ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ ለእነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው።
15በዚህም ሕጉ የሚጠይቃቸው ድርጊቶች በልቦናቸው መጻፋቸውን ያሳያሉ። ሃሳባቸው ሲከሳቸው ወይም ሲደግፋቸው ኅሊናቸው ደግሞ ለራሳቸውና
16ለእግዚአብሔር ይመሰክራል። ይህም እኔ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደምሰብከው ወንጌል ሰዎች ሁሉ በስውር ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር በሚፈርድበት ቀን በዚያን ጊዜ ይሆናል።
17በሕጉ በመመራትህ አይሁዳዊ ነኝ ትላለህ፥ በሕጉ ትደገፋለህ፥ በእግዚአብሔር በመመካት ደስ ትሰኛለህ፥
18ፈቃዱን ታውቃለህ፥ ከእርሱ ውጪ የሆኑትን ነገሮች መርምረህ ትረዳ ይሆናል።
19አንተ ራስህ የዕውሩ መሪ፥ በጨለማ ላሉት ብርሃን፥
20የሰነፎች አስተማሪ፥ የሕጻናትም መምህር በመሆንህ በሕግ የእውቀትና የእውነት መልክ እንዳለህ ትታመን ይሆናል።
21እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?
22አታመንዝር የምትል አንተ ታመነዝራለህን? ጣዖታትን የምትጸየፍ ቤተመቅደሶችን ትዘርፋለህን?
23አንተ በሕጉ በመመካት የምትደሰተው ሰው ሕጉን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ትንቃለህን? ይህ ልክ "በእናንተ
24ምክንያት በአሕዛብ መካከል የእግዚአብሔር ስም ይናቃል" ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
25ሕጉን ብትፈጽም በርግጥ መገረዝ ይጠቅማል፥ የሕጉ ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይሆናል።
26እንግዲህ ያልተገረዘው ሰው የሕጉን ትዕዛዛት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ አይቆጠርለትምን?
27በፍጥረቱ ያልተገረዘው ሰው ሕጉን ቢፈጽም አይፈርድባችሁምን? ይህም እናንተ ቅዱሳት መጻሕፍትና መገረዝ እያላችሁ ሕጉን ተላለፊ ስለሆናችሁ ነው።
28በውጫዊ ማንነቱ ብቻ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ አይደለም፥ የሥጋ ውጫዊ መገረዝ ብቻም መገረዝ አይደለም።
29ነገር ግን በውስጣዊ ማንነቱ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በፊደል ሳይሆን በመንፈስ በልብ የተደረገው ነው። እንዲህ ላለ ሰው ከሰዎች ሳይሆን ከእግዚአብሔር ምስጋና ይሆንለታል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።