መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እንግዲህ ብርቱዎች የሆንን እኛ የደካሞቹን ድካም ልንሸከም እንጂ ራሳችንን ብቻ ልናስደስት አይገባም።
2መልካም ነውና እንድናንጸው እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ።
3ምክንያቱም ክርስቶስ እንኳን እራሱን ደስ አላሰኘም። ይልቁንም «አንተን የሰደቡበት ስድብ በኔም ላይ ደረሰ» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
4አስቀድሞ የተጸፈው ሁሉ በትዕግስትና በቅዱሳት መጽሀፍት እየተበረታታን ድፍረት እንድናገኝ ለትምህርታችን ተጽፎአል።
5እንግዲህ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ ለእርስ በእርሳችሁ በክርስቶስ አንድ ልብ ይስጣችሁ።
6በአንድ ልብና በአንድ አፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታመስግኑ ይህን ያድርግ።
7ልክ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ።
8ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ። ይህን ያደረገው ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ ሊያጸና
9አህዛብ ደግሞ ስለምህረቱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ነው። ይህም «በአህዛብ መካከል አመሰግንሀለሁ፣ለስምህም እዘምራለሁ» ተብሎ በተጻፈው መሰረት ነው።
10እንደገናም ደግሞ «እናንተ አህዛብ ከህዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ» ይላል።
11ደግሞም እንደገና «አህዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑት» ይላል።
12ኢሳያስ ደግሞ «አህዛብን ሊገዛ የሚነሳ የእሴይ ሥር ይወጣል፥ አህዛብም በእርሱ ይመካሉ።» ይላል።
13በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ ትሞሉ ዘንድ የተስፋ አምላክ በማመናችሁ ምክንያት በደስታና በሰላም ሁሉ ይሙላችሁ።
14ወንድሞቼ ሆይ እናንተ ራሳችሁ በመልካምነትና በእውቀት እንደተሞላችሁ እርስ በእርሳችሁም ልትማማሩ እንደምትችሉ ስለእናንተ ተረድቻለሁ።
15ነገር ግን ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ስጦታ ስለአንድ ጉዳይ ላሳስባችሁ በድፍረት ጽፌላችኋለሁ።
16ይኸም ስጦታ የእግዚአብሔርን ወንጌልን እንደ ካህን እንዳቀርብላቸው ወደ አህዛብ የተላክሁ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ መሆኔ ነው። ይህን ማድረግ ያለብኝ የአህዛብ መስዋዕት ተቀባይነት እንዲያገኝና በመንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እንዲቀርብ ነው።
17እንግዲህ ደስታዬ በክርስቶስ ኢየሱስና ከእግዚአብሔር በሚሆኑ ነገሮች ነው።
18አህዛብ ወደ መታዘዝ እንዲመጡ ክርስቶስ በእኔ ካከናወነው ነገር በቀር ስለምንም ነገር ለመናገር አልደፍርም። እነዚህም ነገሮች በቃልና በሥራ
19በምልክትና በድንቆች ኃይል በመንፈስ ቅዱስም ኃይል የተከናወኑ ናቸው። ይህም በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እስከ አልዋሪቆን ድርስ የክርስቶስን ወንጌል በሙላት እንዳደርስ ነበር።
20በዚህ መንገድ ፍላጎቴ ወንጌልን መስበክ ነው፥ ነግር ግን የምሰብከው በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልገነባ የክርስቶስ ስም በሚታወቅበት አካባቢ አይደለም።
21ይህም «ስለእርሱ ያልተነገራቸው ያዩታል፥ ያልሰሙም ያስተውላሉ» ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።
22ስለዚህም ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ እንቅፋት ገጠመኝ።
23አሁን ግን በዚህ ባሉ ክልሎች እንብዛም የምሰራው ነገር የለኝም ወደ እናንተም ለመምጣት ለበርካታ ዓመታት ስናፍቅ ነበር።
24ስለሆነም ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ የሚያሰኝ ጥቂት ጊዜ አሳልፌ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ወደናንተ ጎራ ብዬ እንደማያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
25አሁን ግን በጌታ ያመኑትን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ።
26ምክንያቱም በመቄዶኒያና በአካይያ ያሉ አማኞች በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች መካከል ለሚገኙ ድሆች የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ በደስታ ፈቅደዋል።
27አዎ በደስታ ሊያደርጉት መልካም ፈቃዳቸው ነበር፥ ለነገሩ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናችው። አህዛብ ከእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ከተካፈሉ እነርሱ ደግሞ በቁሳዊ ነገር ሊያገለግሏቸው ይገባል።
28ስለዚህም ይህን ስጦታውን የማድረስ ተግባሬን ከፈጸምኩ በኋላ በእናንተ በኩል ወደ እስፔን አልፋለሁ።
29ወደ እናንተ ስመጣ በክርስቶስ በረከት ተሞልቼ እንደምመጣ አውቃለሁ።
30እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ ስለኔ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አብራችሁኝ እንድትጋደሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በመንፈስ ቅዱስም ፍቅር እለምናችኋለሁ።
31በይሁዳ ካሉ የማይታዘዙ ሰዎች እንድጠበቅ አገልግሎቴም በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩ።
32በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ መጥቼ አብሬያችሁ እንዳርፍ ጸልዩ።
33የሠላም አምላክ ከሁላችሁም ጋር ይሁን። አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።