መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በክንክራኦስ ያለችው ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እህታችንን ፌበንን
2በጌታ እንድትቀበሏት አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ይህንንም ከአማኞች በሚጠበቅ መልኩ አድርጉት፣ የእናንተን እርዳታ በምትፈልግበት በማንኛውም ነገር ከጎኗ ቁሙ። ምክንያቱም እርሷ እራሷ እኔን ጨምሮ ብዙዎችን የምትርዳ ነች።
3በክርስቶስ የአግልግሎቴ አጋሮች ለሆኑት ለአቂላና ለጵርስቅላ ሠላምታ አቅርቡልኝ፥
4እነርሱ ስለእኔ ህይወታቸውን ለአደጋ ያጋለጡ ናቸው። አመሰግናቸዋለሁ፥ እኔ ብቻ ሳልሆን የአህዛብ አብያተክርስቲያናትም ሁሉ ያመስግኗቸዋል።
5በቤታቸው ላለች ቤተክርስቲያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ለክርስቶስ የመጀምሪያው ፍሬዬ የሆነውን የምወደውን አጤኔጦንን ሠላም በሉልኝ።
6ለእናንተ በሥራ ለደከመችው ለማሪያ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
7ዘመዶቼ ለሆኑትና አብረውኝ ታስረው ለነበሩት ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። እነርሱ በክርስቶስ በመሆን የቀደሙኝና ከሐዋሪያት መካከል በመልካም የተመሰከረላቸው ናቸው።
8በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሠላምታ አቅርቡልኝ።
9በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኢሩባኖንና የተወደደውን ስንጣክን ሠላም በሉልኝ።
10በክርስቶስ መሆኑ ለተመሰከረለት ለኤጤሌን ሠላምታ አቅርቡልኝ። የአርስጣባሉን ቤተሰቦች ሠላም በሉልኝ።
11ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሠላምታ አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ ቤተሰቦች መካከል በጌታ ላመኑት ሠላምታ አቅርቡልኝ።
12በጌታ ሥራ ለሚደክሙት ለፕሮፊሞንና ለጢሮፊሞስ ሠላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሥራ በብዙ የምትደክመውን የተወደደች ጠርሲዳን ሠላም በሉልኝ።
13በጌታ ልተመረጠው ለሩፎን እና ለእርሱም ለእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
14አስቀራጦንን፥ አፍለሶንጳን፥ ሄሮሜንን፥ ጳጥሮባን፥ ሄርማንን እንዲሁም አብረዋቸው ያሉትን ወንድምች ሠላም በሉልኝ።
15ለፍሌጎን፥ ለዩልያ፥ ለኔርያ ለእህቱም ለአልንጦን አብረዋቸውም ላሉት በጌታ ላመኑት ሁሉ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
16በተቀደሰ መሳሳም ሠላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ አብያተክርስቲያናት ሁሉ ሠላምታ ያቀርቡላችኋል።
17ወንድሞቼ ሆይ በመካከላችሁ የመለያየትንና የመሰናክል ምክንያት ስለሆኑት ሰዎች እንድታስቡ እለምናችኋለሁ። እነርሱ እናንተ ከተማራችሁት የወጣ ነገር ያስተምራሉና ከእነርሱ ተለዩ።
18እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ክርስቶስን ጌታችንን አያገለግሉም። በለስላሳና በሚያባብል ቃላቸው የየዋሀንን ልብ ያታልላሉ።
19የመታዘዛችሁ ምሳሌነታችሁ ለብዙዎች ደርሷል። ስለዚህም በእናንተ ደስ ይለኛል፥ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር ደግሞ የዋሀን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
20የሠላም አምላክ ሠይጣንን በፍጥነት ከእግራችሁ በታች ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
21የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስና ዘመዶቼ ለቂዮስ፥ኢያሶንና ሱሲጴጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
22ይህን ደብዳቤ በእጄ የጻፍኩ እኔ ጤርጥዮስ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።
23እኔና ቤተክርስቲያንን በሙሉ በቤቱ ያስተናገደን ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው ገንዘብ ያዥ ኤርስጦስ ወንድማችንም ቁአስጥሮስ ሰላም ብለዋችኋል።
25እንግዲህ በወንጌሌ በኢየሱስ ክርስቶስም ስብከት ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ተሰውሮ በነበረውና
26አሁን ግን በዘላለማዊ አምላክ ትዕዛዝ በአህዛብ ሁሉ መካከል በተገለጠውና የእምነት መታዘዝ እንዲገኝ በትንቢታዊ መጽሀፍት አማካኝነት በታወቀው ሚስጥር መሠረት ሊያቆማችሁ ለሚችለው
27ብቻውን ጥበበኛ አምላክ ለሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።