መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።
2መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።
3ከእናንተ ማንም ስለራሱ ሊያስብ ከሚገባው በላይ እንዳያስብ በተሰጠኝ ጸጋ አሳስብለሁ። ይልቁኑም ለእያንዳንዱ ከእግዚአብሔር በተሰጠው እምነት ልክ በጥበብ ሊያስብ ይገባል።
4ልክ እኛ በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች ቢኖሩንም ተግባራቸው ግን ተመሳሳይ አይደለም።
5እንዲሁ እኛም ብዙዎች ሳለን በክርስቶስ አንድ አካል ነን እያንዳንዳችንም አንዳችን የሌላችን የአካል ክፍል ነን።
6በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።
7የአንዱ ስጦታ ደግሞ ቸርነት ማድረግ ከሆነ ቸርነት ያድርግ። የማስተማር ስጦታ ያለው ያስተምር።
8የማጽናናት ስጦታ ያለው ያጽናና፤ የመስጠት ስጦታ ያለው በልግስና ያድርገው፤ የመምራት ስጦታ ያለው በጥንቃቄ ይፈጽመው፤ምህረት የማድረግ ስጦታ ያለው በደስታ ያድርገው።
9ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን። ክፉ የሆነን ነገር ተጸየፉ፤መልካም የሆነውን ያዙ።
10እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።
11ልግምተኞች አትሁኑ፤በመንፈሳችሁ ንቁ ሁኑ ፥ ጌታንም አገልግሉ።
12ስላላችሁ የወደፊት ተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ትዕግስተኞች ሁኑ፥ጸሎታችሁ የማያቋርጥ ይሁን፤
13ቅዱሳንን በችግራቸው እርዱ፤ መልካም ለማድረግ የሚያስችላቹሁን መንገዶች ፈልጉ።
14የሚያሳድዷችሁን ባርኳቸው፥ባርኩ እንጂ አትርገሙ።
15ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
16አንድ ልብ ይኑራችሁ፥ትሁት ሰዎችን ተቀበሉዋቸው እንጂ በትዕቢት አታስቡ። በራሳችሁ አመለካከት ጥበበኞች እንደሆናችሁ አታስቡ።
17ክፉ ላደረገባችሁ ለማንም ክፉ አትመልሱ። በሰዎች ሁሉ ፊት መልካምን ነገር አድርጉ።
18በተቻላችሁ መጠን በእናንተ በኩል ከሰዎች ሁሉ ጋር በሠላም ኑሩ።
19የተወደዳችሁ ሆይ ስለራሳችሁ አትበቀሉ ይልቁኑ ለእግዚአብሔር ቁጣ ዕድል ስጡ።ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ «ጌታ 'በቀል የኔ ነው ብድራትን የምከፍለው እኔ ነኝ' ይላል»።
20«ነገር ግን ጠላትህ ከተራበ መግበው። ከተጠማ ደግሞ የሚጠጣ ስጠው። ይህን ስታደርግ የእሳት ፍም በአናቱ ላይ ትከምራለህ።
21ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።