መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 11

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ታዲያ እግዚአብሄር ህዝቡን ጣላቸውን? ፥በጭራሽ። ምክንያቱም እኔ ራሴ ከቢንያም ወገን የሆንኩ የአብርሀም ዘር እስራኤላዊ ነኝ።
2እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝቡን አልጣላቸውም። ኤልያስ እስራኤልን በመቃወም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደተከራከረ መጽሀፍ የሚለውን አታውቁምን?
3«ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገድለዋል፣ መሰዊያዎችህንም አፍርሰዋል፣ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ሊገድሉኝም እየፈለጉኝ ነው።»
4ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? «ለበዓል ያልሰገዱ ሰባት ሺ ሰዎችን ለራሴ ጠብቄ አቆይቻለሁ።»
5በዚህም በአሁኑ ዘመንም ከጸጋ ምርጫ የተነሳ ትሩፋን አሉ።
6ነገር ግን በጸጋ ከሆነ ከእንግዲህ በሥራ አይደለም።አለዚያ ጸጋ ከእንግዲህ ጸጋ መሆኑ ቀርቷል።
7እንግዲህ ምን ይሁን፣ እስራኤል ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም ፥ የተመረጡት ግን አግኝተውታል፥ የቀሩት ግን ደንዳኖች ሆነዋል።
8ይህም ልክ «እያዩ እንዳያዩ እየሰሙ እንዳይሰሙ እስከ አሁን እግዚአብሔር ያለማስተዋልን መንፈስ ሰጣቸው» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
9ዳዊትም «ገበታቸው መረብ፥ወጥመድ፥የእንቅፋት ድንጋይና የበቀል ይሁንባቸው» ይላል።
10እንዳያዩ አይናቸው ይጨልም፥ ሁልጊዜ ጀርባቸው እንደጎበጠ ይቅር።» ይላል።
11«እስኪወድቁ ድረስ ተሰናከሉ» እላለሁን? ፈጽሞ አይሁን። በቅናት ሊያነሳሳቸው በእነርሱ ውድቀት ለአህዛብ ድነት ሆነ።
12እንግዲህ ውድቀታቸው ለዓለም ሙላት ከሆነ ጉድለታችው ለአህዛብም ሙላት ከሆነ ሙላታቸው እንዴት ታላቅ ይሆን?
13አሁን ለእናንተ ለአህዛብ እናገራለሁ። የአህዛብ ሀዋሪያ እንደመሆኔ በአገልግሎቴ እመካለሁ።
14ምናልባት የገዛ ሥጋዬ የሆኑትን አስቀናና አንዳንዶቹን እናድን ይሆናል።
15የእነኚያ መጣል ለዓለም የመታረቅ ምክንያት ከሆነ ተቀባይነት ማግኘታቸው ከሞት ወደ ህይወት ማምለጥ ካልሆን ምን ሊሆን ይችላል?
16በኩሩ ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ነው። ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፉ ቅዱስ ነው።
17ነገር ግን አንዳንዶቹ ቅርንጫፎች በመሰበራቸው ምክንያት አንተ የበረሀ ወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ ባልወደቁት ቅርንጫፎች መካከል ብትጣበቅና የወይራ ዛፉን ሥር ብልጽግና ተካፋይ ብትሆን
18በቅርንጫፎቹ ላይ አትኩራራ። ብትኩራራ ግን ሥሩ አንተን ተሸከምህ እንጂ አንተ ሥሩን አልተሸከመከውም።
19«ቅርንጫፎቹ ስለተሰበሩ እኔ ተተካሁ» ትላለህ።
20እውነት ነው ባለማመናቸው ምክንያት እነርሱ ተቆርጠው ወድቀዋል አንተ ደግሞ በእምነት ቆመሀል። ፍራ እንጂ ራስህ ከፍ አድርገህ አታስብ።
21እግዚአብሔር ለመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ካልራራ ለአንተም አይራራልህም።
22እንግዲህ የእግዚአብሔርን የምህረት ሥራና ጭካኔ አስተውል። በአንድ በኩል ጭካኔው በወደቁት በአይሁድ ላይ መጣ፥በሌላ በኩል ደግሞ ጸንታችሁ ከቆያችሁ ምህረቱ ወደ እናንተ መጥቷል። አለበለዚያ ግን እናንተም ተቆርጣችሁ ትጣላላችሁ።
23ደግሞም እነርሱ ባለማመናቸው ካልጸኑ እንደገና በዛፉ ላይ ሊተከሉ ይችላሉ። እግዚአብሔር እንደገና በዛፉ ላይ ሊተክላቸው ይችላልና።
24እናንተ መነሻችሁ የበረሀ የወይራ ዛፍ የሆነና ተቆርጣችሁ የነበራችሁ ቅርንጫፎች ከተፈጥሮ ህግ ውጪ በመልካሙ የወይራ ዛፍ ላይ እንደገና ከተተከላችሁ የመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች እነኝህ አይሁድ ወደገዛ ዛፋቸው እንዴት እንደግና አይጣበቁም?
25ወንድሞች ሆይ በራሳችሁ አስተሳሰብ ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ስለዚህ ምስጢር እንግዳ እንድትሆኑ አልፈልግም፡ የአህዛብ ሙላት እስኪፈጸም ድረስ ከፊል ድንዛዜ በእስራኤል ላይ ወድቋል።
26ስለዚህም እስራኤል በሙሉ እንደተጻፈው ይድናሉ። «ከጽዮን ነጻ አውጪ ይነሳል ከያዕቆብም የማይገባ አካሄድን ያስወግዳል።
27ኃጢአታቸውን በማስወግድላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።»
28በአንድ በኩል ወንጌልን በተመለከተ ስለእናንተ የተጠሉ ናቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእግዚአብሔር ምርጫ ምክንያት ስለአባቶቻቸው የተወደዱ ናቸው።
29ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ አይለወጥም።
30እናንተ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ የነበራችሁ አሁን ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ምክንያት ምህረትን አግኝታችኋል።
31ልክ እንደዚያው ዘንድ እነዚህ አይሁድ አሁን የማይታዘዙ ሆነዋል። በውጤቱም ለእናንት በተሰጠው ምህረት እነርሱ ደግሞ እንዲቀበሉ ነበር።
32ምህረቱን ለሁሉ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ሁሉን ባለመታዘዝ ዘግቶታልና።
33ኦ የእግዚአብሔር ጥበብና እውቀት ባለጠግነት ምን ያህል ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር መንገዱም እንዴት ከመታወቅ ያለፈ ነው!
34«የጌታን ልብ የሚያውቅ ማነው? አማካሪውስ የሆነ ማነው?
35ወይስ መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእግዚአብሔር ያበደረ ማነው?»
36ሁሉም ነገር ከእርሱ በእርሱና ለእርሱ ነው። ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።