መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሮሜ 10

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ስለእነርሱ ለእግዚአብሔር የማቀርበው ልመና እንዲድኑ ነው።
2በእውቀት የሆነ ባይሆንም ለእግዚአብሔር እንደሚቀኑ እኔ ራሴ ስለእነርሱ እመሰክራለሁ።
3የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁምና የራሳቸውን ጽድቅ ሊመሰርቱ ይጥራሉ፤ለእግዚአብሔርም ጽድቅ ራሳቸውን አያስገዙም።
4ምክንያቱም ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ ለጽድቅ የሚሆን የህግ ፍጻሜ ነው።
5ሙሴ ከህግ ስለሚመጣ ጽድቅ ሲናገር «ከህጉ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርግ በዚያው ጽድቅ ይኖራል።» ይላልና።
6በእምነት ስለሚሆን ጽድቅ ግን «በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል አትበል (ይህ ክርስቶስን ማውረድ ነውና)
7ወይም ወደ ሲዖል ማን ይወርዳል አትበል (ይህ ክርስቶስን ከሙታን መካከል ማውጣት ነውና)።» ይላል።
8ነገር ግን ቃሉ ምን ይላል? «ቃሉ ለአፍህና ለልብህ ቅርብ ነው።» ይላል። የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው።
9ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ።
10ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።
11ምክንያቱም መጽሀፍ እንደሚል «በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ።
12በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ልዩነት የለም። ያው አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩትም ሁሉ ባለጠጋ ነው።
13የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
14ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ስለእርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል?
15ያለ ሰባኪስ ከየት ይሰማሉ? «በመልካም ነገር የተሞላ ደስታን የሚሰብኩ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው» ተብሎ እንድተጻፈ፣ ሳይላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?
16ነገር ግን ኢሳያስ «ጌታ ሆይ መልዕክታችንን ማን አምኗል» እንዳለው ሁሉም ወንጌልን አልተቀበሉም።
17ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ሲሆን መሰማት ያለበትም የክርስቶስ ቃል ነው።
18ነገር ግን «አልሰሙ ይሆንን?» እላለሁ። በሙሉ እርግጠኝነት ሰምተዋል።«ድምጻቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደርሷል።»
19በተጨማሪም «እስራኤል አያውቁምን?» እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ «ህዝብ ባልሆነ በእሱ በቅናት አነሳሳችኋለሁ። በማያስተውልም ህዝብ በቁጣ አናውጣችኋለሁ» ይላል።
20ደግሞም ኢሳያስ በድፍረት «ላልፈለጉኝ ተገኘሁ ላልጠየቁኝም ተገለጥኩ» ይላል።
21ስለእስራኤል ግን «ለዚህ የማይታዘዝና ደንዳና ህዝብ ቀኑን ሙሉ እጄን ዘረጋሁ» ይላል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።