መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 9

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ አንድን ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ። ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው፤
2እርሱም ጥልቅ የሆነውን ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ከጕድጓዱ በሚወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ወደ ጨለማነት ተለወጡ፤
3ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤የምድር ጊንጦችን ኅይል የመሰለ ኅይል ተሰጣቸው፤
4የምድርንም ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። መጉዳት የነበረባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነው።
5እነርሱንም ቢሆን ለአምስት ወር ለማሰቃየት ብቻ እንጂ የመግደል ሥልጣን አልተሰጣቸውም። የእነርሱም ስቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሰማው ስቃይ ዐይነት ነበር።
6በእነዚያ ቀናት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ነገር ግን አያገኙትም። ለመሞት በብርቱ ይሻሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል።
7አንበጦቹ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነበሩ። በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር።
8የሴቶች ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው። ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር።
9የብረት ጥሩር የሚመስልጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።
10እንደ ጊንጥ መንደፊያ ያለው ጅራት ነበራቸው። ሰዎችንም በጅራታቸው ባለ መንደፊያ ለአምስት ወር ለመጉዳት ስልጣን ነበራቸው።
11በእነርሱም ላይ የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ የሆነ ንጉሥ ነበራቸው። ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጶሊዮን ይባላል፥
12የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ልብ በል! ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ጥፋቶች ይመጣሉ።
13ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሰራው መሰዊያ ከቀንዶቹ ድምጽ ሲወጣ ሰማሁ።
14ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ «በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው» አለው።
15ለዚያ ሰዓትና ለዚያ ቀን ለዚያ ወርና ለዚያ ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራት መላእክት የሰዎችን አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ።
16የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።ቍጥራቸውንም ሰማሁ።
17ፈረሶቹና በፈረሶቹ ላይ የሚጋልቡ በራእይ ያየኋቸው በዚህ ዐይነት ነበር፥ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት (ጥቁር ሰማያዊ)፣ እንደ ዲንም ቢጫ ነበር፥ የፈረሶቹ ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር።
18በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ማለትም ከአፋቸው በወጣው እሳት፤ ጢስና ዲን የሰዎች አንድ ሦስተኛ ተገደለ።
19የፈረሶቹ ኃይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፥ ምክንያቱም ጅራታቸው እባብ ይመስላል፥ ራስ አላቸው፥ ሰውን የሚጎዱትም በእርሱ ነበር።
20በእነዚያ መቅሰፍቶች ከመሞት የተረፉት ሰዎች ከክፉ ሥራቸው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወር፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ፣ ማየት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖታት ማምለክንም አልተዉም።
21እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነት ወይም ከሟርት፥ ከሴስኛነትና፥ ከሌብነት ንስሓ አልገቡም።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።