1በጉ ሰባተኛውን ማህተም በፈታ ጊዜ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሆነ፤
2ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት የቆሙ ስባት መላዕክትን አየሁ፡፤ሰባት መለከቶችም ተሰጣቸው።
3ሌላም መልኣክ መጣ፤በእጁም ከወርቅ የተሰራ ጥና ይዞ ነበር።እርሱም በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቅ በተሰራ መሰዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
4የእጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሄር ወጣ፤
5መልአኩም ጥናውን ወስዶ ከመሰዊያው በወስድው እሳት ሞላው ከዚያም በኃላ ወደ ምድር ወረወረው፤የነጎድጛድ ድምጽ፤መብረቅ፤የምድር መናወጥም ሆነ።
6ሰባት መለከቶችን የያዙ ስባት መላዕክት መለከቶቻቸውን ለመንፋት ተዘጋጁ።
7የመጀመሪያውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ደም የተቀላቀለበት እሳትና በረዶ ሆነ። ይህም ወደ ምድር ተጣለ፤ ከዚህም የተነሣ የምድርም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
8ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር ወደ ባህር ተጣለ፤ የባህር አንድ ሦስተኛ ወደ ደም ተለወጠ።
9በባህር ውስጥ ካሉ ህያዋን ፍጥረታት አንድ ሦስተኛ ሞቱ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ተደመሰሱ።
10ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች አንድ ሦስተኛ በውሃ ምንጮች ላይ ነው።
11የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውኆችም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ። ከውሃው መራራነት የተነሳ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
12አራተኛውም መልአክ መልከቱን ነፋ፤የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ። ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛ ጨለመ፤ በዚህም ምክንያት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛው ያለ ብርሃን ሆነ።
13እነሆ በሰማይ መካከል ሲበርር የነበር አንድ ንስር በታላቅ ድምጽ፤ ሦስቱ መላእክት የቀሩትን መለከቶች ስለሚነፉ «በምድር ላይ ለሚኖሩ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!» ሲል ሰማሁ።