መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 6

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
2አየሁም ፤እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ባላዩ ላይ የተቀመጠውም ቀስት ይዞ ነበር፤አክሊልም ተሰጠው። እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ድል ይነሳ ዘንድ ወጣ።
3በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር«ና!» ሲል ሰማሁ።
4ከዚያም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤በፈረሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርስ ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲያስወግድ ሥልጣን ተሰጠው፤ትልቅ ሰይፍም ተሰጠው።
5በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር «ና!» ሲል ሰማሁ፤ ጥቁር ፈረስ አየሁ፤በፈረሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።
6ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን የመጣ የሚመስል ድምፅ፥«አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፥ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ነገር ግን ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ» ሲል ሰማሁ።
7በጉ አራተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ የአራተኛው ሕያው ፍጡር ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
8ከዚያም በኋላ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤በላዩም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ተብሎ ይጠራ ነበር፤ሲኦልም ይከተለው ነበር። ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ በሰይፍ፥በረሃብ፥ በበሽታ፥በዱር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።
9በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ።
10እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር።
11ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።
12በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ አየሁ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ፀሐይም እንደ ጥቁር ጨርቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ እንደ ደም ቀላች።
13የበለስ ዛፍ ኀይለኛ ነፋስ በሚወዘውዛት ጊዜ በላይዋ ያለ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ ሁሉ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።
14ሰማይም እንደ ብራና እየተጠቀለለ ተወገደ፤ እያንዳንዱ ተራራና ደሴት ከስፍራው ተነቀለ።
15ከዚያም በኋላ የምድር ነገሥታት፥ታላላቅ ሰዎች፥ የጦር መኮንኖች፥ ሀብታሞች፥ብርቱዎች፥ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ።
16ለተራሮችና ለዐለቶችም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤«በላያችን ላይ ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት፥ከበጉም ቁጣ ሰውሩን
17ታላቁ የቁጣቸው ቀን ስለ መጣ ማን መቆም ይችላል?»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።