መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በዙፋኑም ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ከፊትና ከጀርባ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሓፍ አየሁ።
2አንድ ብርቱ መልአክ፥«መጽሓፉን ሊከፍት፥ ማኅተሙን ሊፈታ የተገባው ማን ነው?» ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
3በሰማይ ቢሆን በምድር ወይም ከምድር በታች መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ ማንም አልቻለም።
4መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ የተገባው ማንም ስላልተገኘ፥አምርሬ አለቀስሁ።
5ነገር ግን ከሽማግሌዎች አንዱ፥«አታልቅስ፤እነሆ! ከዳዊት ሥር፥ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ መጽሓፉን ይከፍትና ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል» አለኝ።
6በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንዲሁም በሽማግሌዎች መካከል አንድ ታርዶ የነበረ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ። እርሱም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤እነዚህም በምድር ሁሉ ላይ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።
7ሄዶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልል መጽሓፉን ወሰደ።
8ጥቅልል መጽሓፉንም በሚወስድበት ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገና እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበት የወርቅ ዕቃ ይዘው ነበር።
9እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።
10አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»
11ከዚያም በኋላ ስመለከት፥በዙፋኑ፥በሕያዋኑ ፍጡራን እና በሽማግሌዎች ዙሪያ የብዙ መላእክት ድምፅ ሰማሁ፤ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።
12እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።
13በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤
14አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፥«አሜን» አሉ፤ሽምግሌዎችም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።