1ከዚህ በኃላ የጥልቁ መክፈቻ ያለው አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በእጁም ትልቅ ሰንሰለት ይዞ ነበር።
2ዘንዶውን ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህ ዘንዶ ዶያብሎስ ሰይጣን የተባለው የቀድሞው እባብ ነው።
3ወደ ጥልቁ ጣለው፤ ዘግቶም በእርሱ ላይ ማኅተም አደረገበት። ይህን ያደረገው ሺህ ዓመቱ እስኮፈጸም ድረስ ከእንግዚህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ነው። ከዚያ በኋላ ለአጭር ጊዜ መፈታት ይኖርበታል።
4ከዚያም ዙፋኖች አየሁ። ዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው ነበር። ለኢየሱስና ለእግዚአብሔር ቃል ምስክር የተሰየፉ ሰዎችን ነፍሶችንም አየሁ። ለአውሬው ወይም ለምስሉ አልሰገዱም፤ ምልክቱም ግንባራቸው ወይም እጃቸው ላይ እንዲያረግ አልፈቀዱም። ከሞት ተነሥተው፣ ለሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር ነገሡ።
5የተቀሩት ሙታን ግን ሺሁ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ከሞት አልተነሡም። ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።
6በመጀመሪያው ትንሣኤ ድርሻ የሚኖራቸው ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው! እነዚህን በመሳሰሉት ላይ ሁለተኛው ሞት ኅይል አይኖረውም። የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
7ሽው ዓመት ካበቃ በኃላ ሰይጣን ከእስራት ይፈታል።
8በአራቱ የምድር ማእዘን ያሉ ሕዝቦች ማለትም ጎግና ማጎግን ወደ ጦርነት ለማምጣት እያሳተ ወደ ጦርነት ለማምጣት ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ያህል እጅግ ብዙ ነው።
9እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄደው የቅዱሳንን ሰፈር፣ እንዲሁም የተወደደችውን ከተማን ከበቡ። ሆኖም፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።
10እነርሱን ያሳሳተው ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወደ ተጣለበት በዲን ወደሚነደው የእሳት ባሕር ተጣሉ። ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሰቃያሉ።
11ከዚያም አንድ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በላዩ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፣ ሆኖም፣ መሄጃ ቦታ አልነበራቸውም።
12በዙፋኑ ፊት መታን፣ ታላላቆችና ታናናሾች ቆመው አየሁ፤ መጽሕፍትም ተከፈቱ። ከዚያም የሕይወት መጽሐፍ የተባለ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ። መታንም መጻሕፍቱም ውስጥ በተመዘገበው መሠረት እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው
13ባሕር ውስጡ ያሉ ሙታንን ሰጡ። ሞትና ሲኦል ውስጣቸው ያሉትን ሙታን ስጡ፤ ሙታንም እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው።
14ሞትና ሲኦል ወደ እሳቱ ባሕር ተጣሉ። የእሳቱም ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።
15ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ባሕር ተጣለ።