መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 19

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ የበዙ ሰዎች ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው።
2በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ ስለ ፈረደባት ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው። እርሷ ያፈሰሰችውን የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።
3በድጋሚ “ሃሌ ሉያ፤ ጢስዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም ከእርሷ ይወጣል” በማለት ተናገሩ።
4ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አሜን ሃሌ ሉያ!” በማለት ዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰገዱ።
5ከዚያ በኋላ፣ “ታናናሾችም ታላላቆችም እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።
6ከዚያም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውሆች ድምፅና የብርቱ ነጎድጓድ የሚመስል ድምፅ እንዲህ አለ፤
7ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሙሽራዋም ራስዋን ስላዘጋጀች፤ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ፤ ክብርንም እንስጠው።”
8ደማቅና ቀጭን ንጹሕ ልብስ እንድትለብስ ገሰጣት። ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳኑ የጽድቅ ሥራ ነው።
9መልአኩም፣ “ወደ በጉ ሰርግ እንደመጡ የተጋበዙ ሰዎች የተባረኩ ናቸው ብለህ ጻፍ” አለኝ። በተጨማሪም፣ “እነዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው” አለኝ።
10እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከአንተና ስለ ኢየሱስ የተሰጠውን ምስክር ከያዙ ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ። ልችእግዚአብሔር ስገድ፤ ስለ ኢየሱስ የተሰጠው ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አልኝ።
11ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ ተመለከትኩ ፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ ይባላል። በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋል።
12ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ ራሱም ላይ ብዙ አክሊሎች ነበሩ። ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም እርሱ ላይ ተጽፎ ነበር።
13ደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል።
14ቀጭን፣ ነጭና ንጹሕ ልብስ የለበሱ ሠራዊት በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።
15ከአፉም ሕዝቦችን የሚመታበት የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ በብረት በትር ይገዛቸዋል። ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።
16ልብሱና ጭኑ ላይ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ የሚል ስም ተጽፎበት ነበር።
17አንድ መልአክ ፀሐይ ላይ ቆሞ አየሁ። እርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ኑ፣ ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ግብዣ ተሰብሰቡ።
18መጥታችሁ የነገሥታትን፣ የጦር አዛዦችን፣ ሥጋ የኅያላንን ሥጋ፣ የፈረሰኞችንና በላያቸው የተቀመጡትን ሥጋ፣ የጌቶችን የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፣ የሰዎችን ሁሉ ሥጋ ብሉ።”
19አውሬውንና ከእርሱም ጋር የምድር ነገሥታትንና ሰራዊታቸውን አየሁ። ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነበረውና ከሰራዊቱ ጋር ውጊያ ለመግጠም ተዘጋጅተው ነበር።
20እነሆ አውሬው ተያዘ፤ ከእነርሱም ጋር በእርሱ ፊት ምልክቶችን የሚያደርገው ሐሰተኛ ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች አማካይነት የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳሳተ። ሁለቱም በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር በሕይወት እያሉ ተጣሉ።
21የተቀሩትም ፈረስ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ። ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።