1“በኤፌሶን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ‘ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅመቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፤
2‘ሥራህን፣ ትዕግሥትህንና ጽናትህን አውቃለሁ። ክፉ ሰዎችን መታገሥ አለመቻልህንም አውቃለሁ። ሐዋሪያት ሳይሆኑ “ሐዋሪያት ነን” የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸውም አውቃለሁ።”
3በትዕግሥት እንደ ጸናህ፥ስለ ስሜ ብዙ መከራ ቢደርስብህም እንዳልደከመህ አውቃለሁ።
4ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ይኽውም የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃል።
5እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ ለይተህ እወቅ፤ንስሓ ግባ፤ቀደም ሲል ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። ንስሓ ካልገባህ እመጣብሃለሁ፤መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ።
6ነገር ግን ይህ መልካም ነገር አለህ፤ እኔ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃል።
7ጆሮያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ። ድል ለሚነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው የሕይወት ዛፍ የመብላትን መብት እሰጠዋለሁ።”
8«በሰምርኔስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ መጀመሪያም መጨረሻም የሆነው የእርሱ ቃሎች ናቸው፤ሞቶ የነበረው፥እንደ ገና ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፤
9'"መከራህንና ድኽነትህንም አውቃለሁ፤ነገር ግን ባለጠጋ ነህ፤የሰይጣን ማኅበር ሆነው እያለ፥አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
10ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
11ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለው ይስማ። ድል የሚነሻ በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።
12«በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ካለው የተነገሩ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤
13'"የሰይጣን ዙፋን ባለበት በዚያ እንደምትኖር አውቃለሁ፤ነገር ግን ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ መካከል በተገደለው በታማኙ ምስክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
14ነገር ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው ማሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን የመከረው የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ።
15እንደዚሁም የኒቆላውያንን ትምህርት አጥብቀው የያዙ ሰዎች እንኳ በአንተ ዘንድ አሉ።
16ስለዚህ ንስሓ ግባ፤አለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ከአፌም በሚወጣው ሰይፍ አዋጋቸዋለሁ።
17ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤እንደዚሁም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈብትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።>
18በቲያጥሮን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “የእሰት ነበልባል የመሰሉ ዐይኖችና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።
19ሥራህን፣ ፍቅርህንና እምነትህን፣ አገልግሎትህንና በትዕግሥት መጽናትህን አውቃለሁ። አሁን በቅርቡ ያደረግኸው ቀድሞ ካደረግኸው የበለጠ መሆኑን አውቃለሁ።”
20ነገር ግን የምነቅፍብህ አንድ ነገር አለኝ፤ራሷን ነቢይት ብላ የምትጠራውን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል። ይህች ሴት በትምህርትዋ አገልጋዮቼ ሴሰኛ እንዲሆኑና ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉ ታስታቸዋለች።
21ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር ፤ይሁን እንጂ ከርኩሰትዋ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም።
22እነሆ በሥቃይ አልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩት እርስዋ ከፈጸመችው ነገር ንስሓ ካልገቡ በስተቀር በከባድ ሥቃይ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
23በሞት እቀጣለሁ፤በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሰውን ሐሳብና ፍላጎትን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ። ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላለሁ።
24ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉ እንዲሁም አንዳንዶች የሰይጣን ጥልቅ ምስጢር ነው የሚሉትን ነገር ለማታውቁ በትያጥሮን ለምትኖሩ ለቀራችሁት ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም።>
25ሆኖም እስክመጣ ድርስ ያላችሁን ነገር አጸንታችሁ ጠብቁ።
26ለሚነሣውና እስከ መጨረሻው እኔ የደረግሁትን ለሚያደርግ በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።
27በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላም ዕቃ የደቃቸዋል።
28እኔ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።
29ጆሮ ያለው መንፈስ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ።”