1«በሰርዴስ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ በማለት ይናገራል፤«ሥራህን ዐውቃለሁ፤ሕያው እንደሆንህ የሚገልጽ ዝነኛ ስም አለህ፤ነገር ግን ሞተሃል።
2ሥራህን በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆኖ ስላላገኘሁት ንቃ፤ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
3እንግዲህ ምን እንደተቀበልህና ምን እንደሰማህ አስታውስ፤ጠብቀው፤ንስሓም ግባ። ነገር ግን ባትነቃ ፥እንደ ሌባ እመጣለሁ፤በምን ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም።
4ነገር ግን በሰርዴስ ልብሳቸውን ያላቆሸሹ ጥቂት ሰዎች አሉ። የተገባቸውም ስለ ሆነ፥ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
5ድል የሚነሳ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ ፈጽሞ አልደመስሰውም፤ይልቁን በአባቴና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሰክራለሁ።
6ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ይሚናገረውን ስማ።»
7«በፊላደልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥የሚከፍት እርሱ የከፈተውን ማንም የማይዘጋ፥የሚዘጋ እርሱ የዘጋውን ማንም ሊከፍት የማይችል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፤
8ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።
9እነሆ፤አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉት እነዚያ ከሰይጣን ማኅበር የሆኑት ውሸተኞች ናቸው። እነርሱንም እኔ እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ መጥተው በእግርህ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
10በትዕግሥ እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ ፥በምድር የሚኖሩትን ይፈትን ዘንድ በዓለም ላይ ሁሉ ሊመጣ ካለው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
11በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።
12ድል የሚነሻውን በአባቴ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በፍጹም አይወጣም። እርሱ ላይ የአምላኬን ከተማ ስም፣ ማለት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትወጣውን የአዲሲቱ ኢዩሳሌምን ስም ደግሞ አዲሱ ስሜን እጽፋለሁ።
13ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን የስማ።”
14«በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ይህም በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ገዥ እንዲሁም እውነተኛና ታማኝ ምስክር ከሆነው ቃሉም አሜን ከሆነው የተነገረ ነው፤
15ሥራህን አውቃለሁ፤በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም ይሆን ነበር።
16እንግዲህ ትኩስ ወይም በራድ ሳትሆን በመካከል ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
17«እኔ ሀብታም ነኝ፤ብዙ ገንዘብ አለኝ፤የጎደለኝ ምንም ነገር የለም» ትላለህ፤ነገር ግን እጅግ ጎስቋላ፥ምስኪን፥ድኻ፥ዕውርና የተራቆትህ እንደሆንህ አታውቅም።
18ሀብታም ትሆን ዘንድ በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥የራቁትነትህን ሐፍረት ለመሽፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥አጥርተህ ለማየትም ዐይንህን እንድትኳል እመክርሃለሁ።
19እኔ የምወዳቸውን እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ እቀጣቸዋለሁ፤ አስተምራቸዋለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ንስሓም ግባ።
20እነሆ፤በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምጼን ሰምቶ ቢከፍትልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
21እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ።
22መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።»