መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ይህ ፈጥኖ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ራእይ ነው። እርሱም ይህን ራእይ መልአኩን ወደ አገልጋዩ ወደ ዮሐንስ በመላክ እንዲታወቅ አድርጓል።
2ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል በሚመለከት ስላየው ማንኛውንም ነገር እና ክርስቶስን በሚመለከት ስለተሰጠው ምስክርነት ተናግሯል።
3ዘመኑ ስለ ቀረበ ፥ የዚህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው፤እንዲሁም የሚሰሙት ሁሉ በውስጡም የተጻፈው ን ነገር የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።
4ከዮሐንስ፥በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ካለው፥ከነበረው፥ወደፊትም ከሚመጣውና በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች
5እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥
6አባቱ ለሆነው እግዚአብሔር መንግሥትና ካህናት እንሆን ዘንድ ላደረገን ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።
7እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን።
8ጌታ እግዚአብሔር፥«አልፋና ኦሜጋ፥ ያለሁና የነበርሁ፥ወደፊትም የምመጣው ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ» ይላል።
9እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
10በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ።
11ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ ከዚያም በኤፌሶን፥ በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥ በትያጥሮን፥ በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።
12ይናገረኝ የነበረው የማን ድምፅ እንደ ሆነ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወር በምልበትም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ።
13በመቅረዞቹም መካከል እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰና ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ የሰው ልጅ የሚመስለው ነበር።
14ራሱና ጸጉሩ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር ማለትም እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ፤ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል፥
15እግሮቹም በእቶን እሳት እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፥ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውኃ ድምፅ ነበር።
16በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ፊቱም ጸሐይ በሙሉ ኀይልዋ ስታበራ የምታበራውን ያህል ያበራ ነበር።
17ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ፤ እርሱም ቀኝ እጁን በእኔ ላይ በመጫን እንዲህ አለኝ፤ «አትፍራ፤እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው
18ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።
19ስለዚህ ያየኽውን፥አሁን ያለውን ሁኔታና ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ነገር ጻፍ።
20በቀኝ እጄ ያሉት አንተም ያየሃቸውን የሰባቱን ከዋክብትና የሰባቱን የወርቅ መቅረዞች ምስጢር በተመለከተ ትርጉሙ ይህ ነው፤ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ሲሆኑ፥ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።