መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 18

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚህ በኋላ ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። ታላቅ ሥልጣንም ነበረው፤ ምድርም በክብሩ አበራች።
2በታላቅ ድምፅም ጮኾ እንደኢህ አለ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ ማደሪያ፣ የማንኛውም ርኩስና ጠያፍ ወፍ መጠጊያ ሆነች
3ሕዝቦች ሁሉ ቁጣ በሚያመጣበት የዝሙቷ ወይን ጠጅ ሰክረዋል። የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረዋል። የምድር ነጋዴዎች በምቾት ኑሮዋ በልጽገዋል።”
4ሌላ ድምጽም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአትዋ እንዳትካፈሉ የማመጣበትንም መቅሠፍት እንዳትቀበሉ ከእርሷ ውጡ።
5ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ተከምሯል እግዚአብሔር ክፉ ሥራዋን አስታውሷል።
6በሰጠችው መጠን ስጧት፤ ባደረገችው መጠን ዕጥፍ አድርጉባት እርሷ በቀካቀከችው ጽዋ መጠን፣ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።
7እርሷ ራስዋን እንዳከበረችውና በምቾት በኖረችው መጠን፣ የዚያኑ ያህል ስቃይና ሐዘን ስጧት እርሷ በልቧ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጫለሁ መበለትም አይደለሁም ሀዘንም አይደርስብኝም’ ብላለች።
8ስለዚህ፣ መቅሠፍቶችዋ በእብንድ ቀን ይደርሱባታል፣ ሞት፣ ሐዘንና ረሐብ ይመጡባታል። በእሳት ትቃጠላለች፤ እርሷ ላይ የሚፈርድ ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነው”
9ከእርሷ ጋር ያመነዘሩና ቅጥ ያጣ ሕይወት የኖሩ፣ የቃጠሎዋ ጭስ ሲወጣ ሲያዩ ስለ እርሷ እየጮኹ ያለቅሳሉ።
10ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው፣ “ታላቂቱ ከተማ፣ አንቺ ብርቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ቅጣትሽ መጥቷልና ወዮልሽ ወዮልሽ” ይላሉ።
11ከእንግዲህ ሸቀጧን የሚገዛ ስለማይኖር የምድር ነጋዴዎች ለእርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝኑላታል፤
12ሸቀጦችዋ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቁ፣ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ጨርቅ፣ ሐር ጨርቅ፣ ቀይ ጨርቅ፣ ማንኛውም ዓይነት ጣፋጭ ሽታ ያለው እንጨት፣ ማንኛውም ከዝሆን ጥርስ የተሠራ ዕቃ፣ ማንኛውም ከከበረ ድንጋይ የተሠራ ዕቃ፣ ነሐስ፣ ብረት፣ እብነ በረድ
13ቀረፋ፣ ቅመም፣ የሚሸር እንጨት፣ ከርቤ፣ ዕጣን፣ ወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ንጹሕ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶችና ሰረገሎች ባሪያዎችና የሰዎች ነፍሶች ናቸው።
14አጥብቀሽ የተመኘሻቸው ነገሮች ከአንቺ አምልጠዋል። ምቾትና ውበትሽ ጠፍተዋል ከእንግዲህም አይገኙም።
15በእርሷ የበለጸጉ እነዚህን ዕቃዎች የሚነግዱ ሰዎች ሥቃይዋን በመፍራት ከእርሷ ርቀው በመቆም በታላቅ ድምፅ ያለቅሳሉ
16እንዲህም ይላሉ “ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ትለብስ ለነበች፤ በመርቅ፣ በከበረ ድንጋይና በዕንቁ ታጌጥ ለነበረች ታላቂቱ ከተማ ወዮ ወዮ!”
17በእብንድ ሰዓት ያ ሀብት ሁሉ ጠፍቷል። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፣ መርከበኞችና በባሕር ላይ የሚሠሩ ሁሉ ርቀው ቆሙ።
18ያቀጠሎዋን ጭስ ሲመለከቱ፣ “ ታላቂቱን ከተማ የሚመስላት ማነው?” እያሉ ጮኹ።
19በራሳቸውም ላይ ዐመጽ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ፣ መርከቦች ያሏቸውና በእርሷ ሀብት የበለጸጉ ሁሉ ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ስለ ወደመች ወዮላት ወዮላት” አሉ።
20“ ሰማይ ሆይ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ስለ እናንተ እርሷ ላይ ፈርዷልና እናንት ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ!”
21ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ ታላቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስልን ድንጋይ እንዲህ በማለት ወደ ባሕር ወረወሬ፣ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን በዚህ ሁኔታ በኅይል ተገፍታ ወደ ባሕር ትጣላለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጨርሶ አትታይም
22የበገና ደርዳሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንትና መለኮት ነፊዎች ድምፅ ከእንዲህ በአንቺ አይሰማም። ማንኛውንም ዓይነት የጥበብ ሥራ የሚሠራ በአንቺ አይገኝም። የወፍጮ ድምፅም በአንቺ አይሰማም።
23የመብራት ብርሃን፣ ከእንግዲህ በአንቺ አያበራም። የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ በአንቺ አይሰማም። ነጋዴዎችሽ የምድር ልዑላን ነበሩ ሕዝቦችን በመተትሽ አሳስተሻል።
24የነቢያትና የቅዱሳን ደም፣ በዚህ ምድር የተገደሉ ሰዎች ሁሉ ደም በእርሷ ተገኝቷል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።