1ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለን፤ “በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን ታላቂቱ አመንዝራ የፍርድ ቅጣት አሳይሃለሁ፤
2የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረሃል፤ ከዝሙቷ ወይን ጠጅ የምድር ነዋሪዎች ሰክረዋል።”
3መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወስዶኝ፣ የስድብ ስሞች በሞሉበት ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች ሴት አየሁ። አወሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት።
4ሴትዬዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች እንዲሁም በዕንቁዎች አጊጣ ነበር። በእዛም ጸያፍ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።
5ግንባሯም ላይ፣ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ጸያፍ ነገሮች እናት” የሚል ምስጢራዊ ትርጉም ያለው ስም ተጽፎ ነበር።
6ሴትዬዋ በቅዱሳንና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየሁ። ባየኋት ጊዜ በጣም ተደነቅሁ።
7መልአኩ ግን፣ “ለምን ትደነቃለህ? የሴትዮዋንና የተሸከማትን አውሬ (ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉትን አውሬ) ምንነት እነግርሃለሁ።
8ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበረ፤ አሁን የለም፤ ሆኖም በኃላ ከጥልቁ ጉድጓድ ይመጣል። ከዚያም ወደ ጥፋት ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ሰማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ቀድሞ የነበረውን፣ አሁን የሌለውን በኃላ ግን የሚመጣውን አውሬ ሲያዩ ይደነቃሉ።
9ይህ አስተዋይ አእምሮን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴትዬዋ የተቀመጠችባቸው ሰባት ኮረብቶች ናቸው።
10እነርሱም ሰባት ነገሥታት ናቸው። አምስቱ ወድቀዋል፤ አንድሱ አሁንም አለ፤ ሌለው ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ መቆየት ይገባዋል።
11ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የሌለው አውሬ ራሱ ስምንተኛው ንጉሥ ነው ሆኖም፣ ከሰባቱ አንዱም ነው ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
12ያዩኋቸው አሥር ቀንዶች ገና መንግሥት ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ለአንድ ሰዓት ያህል ከአውሬው ጋር እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።
13እነዚህ ነገሥታት ተመሳሳይ ሐሳብ አላቸው፤ ኅይልና ሥልጣናቸውን ሁሉ ለአውሬው ያስረክባሉ።
14በጉን ይዋጋሉ። ይሁን እንጂ፣ በጉ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ በመሆኑ እርሱ ያሸንፋቸዋል የተጠሩት፣ የተመረጡትና ታማኝ የሆኑት ከእርሱ ጋር ድል ይነሣሉ።”
15መልአኩም፣ “አመንዝራዋ ተቀመጣባቸው የነበሩት ያየሃቸው ውሆች ሕዝቦችና ሰዎች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ናቸው” አለኝ።
16ያየሃቸው አሥር ቀንዶች ከአውሬው ጋር አንድ ላይ ሆነው አመንዝራዋን ይጠላሉ። ያጠፏታል፤ ራቁትዋን ያስቀሯታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ ጨርሶ እስክትጠፋ በእሳት ያቃጥሏታል።
17ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ሥልጣናቸውን ለአውሬው ለመስጠት በመስማማት ዕቅዱን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ይህን ሐሳብ በልባቸው ውስጥ አኑሮአል።
18ያይየሃት ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትገባ ታላቂቱ ከተማ ናት።”