1ከዚህም በኃላ ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚፈጽምባቸው የመጨረሻዎቹን ሰባት መቅሰፍት የያዙትን ሰባት መላዕክት አየሁ
2እኔም እሳት የተቀላቀለበት የሚመስል የመስተዋት ባህር አየሁ፤ አውሬውንና የአውሬውን ምስል የስሙንም ቁጥር ድል የነሱትን በባህሩ አጥገብ ቆመው ነበር። እግዚአብሔር የሰጣቸውንም በገና ይዘው ነበር።
3እነርሱም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር «ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ ስራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የእዝቦች ንጉስ ሆይ መንገድህ ትክክልና እውነት ነው።
4ጌታ ሆይ አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ የጽድቅ ስራህ ስለተገለጠ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።»
5ከዚህም በኃላ አየሁ እነሆ የምስክር ድንካን የሆንው ቅድስተ ቅዱሳን በሰማይ ተከፈተ።
6ከቅድስተ ቅዱሳንም ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባት መላዕክት ወጡ፤ የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ ለብሰው ነበር። ደረታቸውንም በወርቅ መታጥቂያ ታጥቀው ነበር።
7ከአራቱ ህያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የውርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላዕክት ሰጣቸው።
8ቅድስተ ቅዱሳኑም ከእግዚአብሔር ክብርና ኃይል የተነሳ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላዕክት የያዙእቸው ስባት መቅሰፍቶች እስኪፈጽሙ ድረስ ማንም ወደ ቅዱሰተ ቅዱሳኑ መገባት አልቻሉም።