መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1አየሁም እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ በፊቴ ቆሞ ነበር። ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
2በሰማይ እንደ ብዙ ውኃ ድምጽና ና እንደታላቅ ነጎድጋድ ድምጽ የመሰለ ድምጽ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምጽ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምጽ ይመስል ነበር።
3እነርሱም በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች በሽማግሌዎችም ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ይህንም መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከአንድ መቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
4እነርሱም ራሳቸውን ከሴቶች ጋር ካላረከሱት ናቸው፤ ራሳቸውንም በግብረ ስጋ ግንኙነት ካለማርከስ ጠብቀዋል። እነርሱ ናቸው በጉ ወደሚሄድበት ሁሉ የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኩራት ለመሆን ከሰዎች መካከል የተዋጁ ናቸው።
5በአንደበታቸውም ሀሰት ተናግረው አያውቁም። ነቀፋም የሌለባቸው ናቸው።
6በምድር ላይ ለሚኖሩ ለህዝብ፤ ለነገድ፤ ለቃንቃና ለወገን ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን የምስራች ቃል የያዘ ሌላ መልዓክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ
7እርሱም በታላቅ ድምጽ «እግዚአብሄርን ፍሩ፤ አክብሩትም። ምክንያቱም የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሳል፤ ሰማይን፤ ምድርን፤ ባህርንና የውሃ ምንጮችን የፈጠረን አምላክ አምልኩ» አለ
8ሌላም ሁለተኛ መልአክ «የዝሙትዋ ፍትወት የሆነውን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለህዝቦች ሁሉ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፤ ወደቀች» እያለ የመጀመሪያውን መልዓክ ተከተለው
9ሌላ ሶስተኛ መለዓክ በታላቅ ድምጽ እንዲህ እያለ ተከተላቸው «ለአውሬውና ለምስሉ ቢሰግዱ ምልክቱን በግምባሩ ወይም በእጁ ቢያደርግ፤
10የእግዚአብሔርን የቁጣ የወይን ጠጅ ይጠጣል፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቁጣው ጽዋ የተዘጋጀ ነው፤ ፅሚጠጣውም ሰው በቅዱሳን መላዕክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል፤
11የስቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ለሊት ዕረፍት የላቸውም።
12የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁና በኢየሱስ የሚያምኑማመኑ ቅዱሳን፤ ትዕግስታቸው የሚታየው እዚህ ላይ ነው።
13ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማሁ «ይህን ጻፍ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው» መንፈስም አዎ ስራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ» ይላል
14አየሁም እነሆ ነጭ ደመና ነበር በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦ ነበር። በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል።
15ከዚህም በኃላ ሌላ መልአክ ከመቅደሱ ወጣ በደመና ላይ የተቀመጠውን በታላቅ ድምጽ «የምድር መከር ደርሶአል የአጨዳ ሰዓትም ቀርቦአል፤ ስለዚህ ማጭድህን ስደድ» አለው።
16በደመናው ላይ የተቀመጠውም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው ምድርም ታጨደች።
17ሌላ መልዓክ ከሰማይ ባለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር።
18በእሳትም ላይ ስልጣን ያለው ሌላ መልዓክ ከመሰዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልዓክ በታላቅ ድምጽ «የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለበሰሉ የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቁረጥ» አለው።
19መልዓኩም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው፤ የምድርንም ወይን ዘለላ ቆረጠ፤ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጭመቂያ ውስጥ ጣለው።
20ከከተማው ውጭ ባለው በወይን መጥመቂያም ተጨመቀ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጋም ወደ ላይ ከፍ ያለና 300 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።