መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 13

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያም አንድ አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ። እርሱም ዐስር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት። በቀንዶቹም ላይ አስር አክሊሎች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድብ ስሞች ነበሩት።
2ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፤ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ይገዛም ዘንድ ዘንዶው የራሱን ኅይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ስልጣን ለአውሬው ሰጠው።
3ከአውሬው ራሶቹ አንዱ ለሞት የሚያበቃ ቁስል እንደነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርስው ቁስል ዳነ፤በዚህም ምክንያት ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ።
4አውሬውም ስልጣኑን በመስጠቱ ሁሉም ለዘንዶው ሰገዱለት «አውሬውን ማን ይመስለዋል? ከእርሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?» እያሉ ለአውሬው ሰገዱለት።
5አውሬውም የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ ለአርባ ሁለት ወራትም ስልጣኑን እንዲያሳይ ተፈቀደለት።
6አውሬው አፉን ከፍቶ እግዚአብሔርን፤ የእግዚአብሔርን ስም፤ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀምረ።
7አውሬው ቅዱሳንን እንዲዋጋ ና፤ ድል እንዲነሳቸውም ስልጣን ተሰጠው። በነገድና በወገን በቃንቃና በህዝብ ሁሉ ላይ ስልጣን ተስጠው።
8ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በታረደው በግ የህይወት መጽሀፍ ያልተጻፈ በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁ ሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ።
9የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
10«የሚማረክ ማንም ቢኖር ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገደል ማንም ቢኖር በሰይፍ ይገደላል» እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግስትና እምነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው።
11ከዚህም በኃላ ሌላ አውሬ ደግሞ ከምድር ሲውጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶች ነበሩት አነጋግሩም እንደ ዘንዶው ነበር።
12የመጀመሪያውን አውሬ ስልጣን ሁሉ በመጀመሪያው አውሬ ፊት ሆኖ ይሰራበት ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለአውሬው እንዲሰግዱለት ያደርጋል፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያድርስ ቁስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።
13እርሱም በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፤
14እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተዓምራት በሰይፍ ቁስሎ የዳነውን የአውሬውን ምስል እንዲሰሩ በማዘዝ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር።
15እርሱም ምስሉ መናገር እንካ እስከሚችል ድረስ እስትንፋስ ለመስጠትና ለአውሬው የማይስግዱትን መግደል ይችል ዘንድ ለማድረግ ስልጣን ተሰጠው።
16እርሱም ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፤ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።
17የአውሬው ስም የሆነው ምልክት ወይም የስሙ ቁጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆን መሸጥ አይችልም ነበር።
18ይህ ጥበብን የሚጠይቅ ነው።የሚያስተውል የአውሬውን ቁጥር ያስላው፤ ቁጥሩም የሰው ቁጥር ነው፤ የውሬውም ቁጥር 666 ነው፤
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።