መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የዮሐንስ ራእይ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በሰማይም ታላቅ ምልክት ታየ ፤ ፀሐይን የለበሰችና ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ያሉት አክሊልም በራስዋ ላይ የደፋች አንዲት ሴት ታየች።
2እርስዋም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ምጥ ይዟትም ተጨንቃ ትጮህ ነበር፥
3እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤እነሆ፤ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፤በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።
4በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣለ፤ዘንዶውም ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ልትወልድ ወደ ተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።
5ሴቲቱም ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጅዋ ግን ወደ እግዚአብሔርና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተወሰደ፤
6ሴቲቱም ወደ ምድረበዳ ሸሽታ ሄደች፤ በዚያም እግዚአብሔር ለ1260 ቀን በክብካቤ ተይዛ እንድትጠበቅ አደረጋት።
7በሰማይም ጦርነት ሆነ። ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ዘንዶውና መላእክቱ መልሰው ተዋጓቸው።
8ነገር ግን ዘንዶው የማሸነፍ ዐቅም አልነበረውም፤ከዚያም ወዲያ እርሱና መላእክቱ በሰማይ የነበራቸውን ስፍራ አጡ።
9ታላቁም ዘንዶ ወደ ምድር ተጣለ፤ እርሱም ሰዎችን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀደመው እባብ ነው።እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
10ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤«አሁን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል፤ሥልጣንም የእርሱ ክርስቶስ ሆኖአል።ምክንያቱም ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ለሊት ሲከሳቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል።
11እነርሱም በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሡት፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና።
12ስለዚህ ሰማይና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርና ባህር ግን ወዮላችሁ፤ ምክንያቱም ጥቂት ጊዜ እንደ ቀረው ዐውቆ ዲያቢሎስ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዷል።
13ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባስተዋለ ጊዜ፤ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት፤
14ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመንም እኩሌታ በክብካቤ ተጠብቃ ወደ ምትኖርበት በምድረ በዳ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ ሁለት የታላቅ ንስር ክንፎች ተሰጧት።
15እባቡ የወንዝ ውሃ የሚያህል ውሃ ከአፉ ተፍቶ ሴቲቱ በጎርፍ እንድትወሰድ ብሎ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
16ነገር ግን ምድር አፍዋን ከፍታ ዘንዶው በአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ በመዋጥ ረዳቻት።
17ከዚያም ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ ከትሩፋን ዝርያዎችዋ ጋር ሊዋጋ ሄደ። እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ስለ ኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩት ናቸው።
18ዘንዶውም በባህር ዳር ባለው አሸዋ ላይ ቆመ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።