1እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጐአልና ለያህዌ አዲስ መዝሙር አቅርቡ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ድል ሰጥተውታል፡፡
2ያህዌ ማዳኑን አሳወቀ ጽድቁንም ለሕዝቦች ሁሉ በግልጽ አሳየ፡፡
3ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን ታማኝነቱንም አሰበ፡፡ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አዩ፡፡
4ምድር ሁሉ ለያህዌ እልል በሉ ውዳሴ አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፡፡
5በገና በመደርደርና በመዝሙር ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ፡፡
6በመለከትና በእምቢልታ ድምፅ በንጉሡ በያህዌ ፊት እልል በሉ፡፡
7ባሕርና በውስጡ ያለው ሁሉ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ
8ወንዞች ያጨብጭቡ ተራሮችም በደስታ እልል ይበሉ፡፡
9ያህዌ በምድር ላይ ለመፍረድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡