1እግዚአብሔር ነገሠ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ፡፡
2ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ ጻድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፡፡
3እሳት በፊቱ ይሄዳል በዙሪያው ያሉ ባላንጣዎቹን ይፈጃል፡፡
4መብረቁ ዓለምን አበራ ምድር ዐይታ ተንቀጠቀጠች፡፡
5ተራሮች ያህዌ ፊት የምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ
6ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ፡፡
7የተቀረጹ ምስሎች የሚያመልኩ፣ በጣዖቶች የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ እናንት አማልክት ሁላችሁ ለእርሱ ስገዱ
8ያህዌ ሆይ፣ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት የይሁዳም ከተሞች ሐሤት አደረጉ፡፡
9ያህዌ ሆይ፣ አንተ በምድር ሁሉ ልዑል ነህና ከአማልክት ሁሉ ይልቅ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ፡፡
10ያህዌን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ! እርሱ የቅዱሳኑን ሕይወት ይጠብቃል ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል፡፡
11ብርሃን ለጻድቃን ሐሤትም ለልበ ቅኖች ወጣ፡፡
12እናንተ ጻድቃን በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ፡፡