መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 99

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ፡፡
2ያህዌ በጽዮን ታላቅ ነው ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡
3ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
4ፍትሕ የምትወድ ኃያል ንጉሥ ሆይ ጽድቅንና ፍትሕን ለያዕቆብ አደረግህ፡፡
5አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
6ሙሴና አሮን ካህናቱ መካከል ነበሩ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል ነበረ እነርሱ ወደ ያህዌ ጸለዩ እርሱም መለሰላቸው፡፡
7በደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ፡፡
8አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ አንተ መለስህላቸው ይቅር ባይ አምላክ ሆንህላቸው ኃጢአታቸውን ግን ቀጣህ፡፡
9አምላካችን ያህዌን አመስግኑ አምላካችን ያህዌ ቅዱስ ነውና በቅዱስ ተራራው ሰገዱ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።