1ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ
2ለያህዌ ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ ማዳኑንንም ዕለት በዕለት ተናገሩ፡፡
3ክብሩን በሕዝቦች መካከል ድንቅ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፡፡
4እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል ከአማልክት ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል፡፡
5የሕዝቦች አማልክት ሁሉ ጣዖቶች ናቸው ያህዌ ግን ሰማያትን ሠራ፡፡
6ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው ብርታትና ውበትም መቅደሱ ውስጥ አሉ፡፡
7የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ለያህዌ ምስጋና ስጡ ክብርንና ብርታትን ለያህዌ ስጡ፡፡
8ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ ስጦታ ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ፡፡
9ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡
10በሕዝቦች መካከል፣ «እግዚአብሔር ነገሠ» በሉ፤ ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፡፡ እርሱ ሕዝቦች ላይ በጽድቅ ይፈርዳል፡፡
11ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሴት ታድርግ፡፡ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ እልል ይበል፡፡
12መስክና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፡፡
13እርሱ ይመጣልና በያህዌ ፊት ይዘምራሉ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡