1ኑ፣ ያህዌን እናመስግን የመዳን ዐለታችን ለሆነው ለእርሱ በደስታ እንዘምር፡፡
2ወደ ፊቱ በምስጋና እንግባ በዝማሬም እናወድሰው፡፡
3ያህዌ ታላቅ አምላክ ነውና ከአማልክትም ሁሉ የበለጠ ታላቅ ንጉሥ ነው፡፡
4የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው፡፡
5ባሕር የእርሱ ነው፤ እርሱ ሠራው እጆቹም የብሱን አበጁ፡፡
6ኑ እናምልከው እንስገድለትም በፈጠረን በያህዌ ፊት እንንበርከክ
7እርሱ አምላካችን ነውና እኛ የመሰማሪያው ሕዝብ የእጁም በጐች ነን፡፡ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ
8«በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመረባም እንዳደረጋችሁት ልባችሁን አታደንድኑት፡፡
9ሥራዬን ቢያዩም አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም፤
10ያንን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቆጣሁት፣ እኔም፣ «ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቁም» አልሁ፡፡
11ስለዚህ፣ «በፍጹም ወደ እኔ ዕረፍቴ ቦታ አይገቡም» ብዬ በቁጣየ ማልሁ፡፡