1በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡
2ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡
3ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛም መቅሠፍት ያድንሃል
4በላባዎቹ ይጋርድሃል በክንፎቹም ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፡፡ ታማኝነቱም ጋሻና መከታ ይሆንልሃል፡፡
5የሌሊትን ሽብር፣ በቀን ከሚወረወር ፍላጻም አትፈራም
6በጨለማ ከሚያደባ ቸነፈር በቀትርም ከሚወርድ መቅሠፍት አትሰጋም፡፡
7በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም፡፡
8በዐይንህ ብቻ ታያለህ የክፉዎችንም መቀጣት ትመለከታለህ፡፡
9አንተ ያህዌን መሸሸጊያ ልዑል አምላክንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና፡፡
10ክፉ ነገር አያገኝህም መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይጠጋም፡፡
11በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፡፡
12እግሮችህ በድንጋይ እንዳይሰናከሉ በእጆቻቸው ያነሡሃል፡፡
13አንበሳና እፉኝት ላይ ትጫማለህ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ፡፡
14ወዶኛልና አታደገዋለሁ በእኔ ተማምኖአልና እጠብቀዋለሁ፡፡
15ይጠራኛል እኔም እመልስለታለሁ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ ድል አቀዳጀዋለሁ፤ አከብረውማለሁ፡፡
16ረጅም ዕድሜ አጠግበዋለሁ ማዳኔንም አሳየዋለሁ፡፡