1ያህዌን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፣ ለስምህ መዘመር መልካም ነው፡፡
2ምህረትህን በማለዳ ታማኝነትህን በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፡፡
3ዐሥር አውታር ባለው በገና ከመሰንቆም ጣዕመ ዜማ ጋር ማወጅ መልካም ነው፡፡
4ያህዌ ሆይ፣ በሥራህ ደስ ስላሰኘኸኝ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ፡፡
5ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው? ሐሳብህ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡
6ደነዝ ሰው ይህን አያስተውልም ሞኝም ይህን አይረዳም፣
7ክፉ ሰዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ ተንኰለኞችም ቢለመልሙ ለዘላለሙ ይጠፋሉ፡፡
8አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም ትነግሣለህ፡፡
9ጠላቶችህ ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ ይጠፋሉ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ፡፡
10እንደ ጐሽ ቀንድ ቀንዴን ከፍ ከፍ አደረግህ በትኩስ ዘይትም ቀባኸኝ፡፡
11ዐይኖቼ የባላንጣዎቹን ውድቀት አዩ ጆሮቼም የክፉ ጠላቶቼን ጥፋት ሰሙ፡፡
12ጻድቃን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ፡፡
13በያህዌ ቤት ተተክለዋል በአምላካችን አደባባይ ይንሰራፋሉ፡፡
14ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ፡፡
15እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤ እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም፡፡