መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

መጽሐፈ መዝሙር 90

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ጌታ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ነህ፡፡
2ተራሮችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ
3ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ «የሰው ልጆች ሆይ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ» ትላለህ፡፡
4ሺህ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈው ትናንት ቀን እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው፡፡
5እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው እንደ ሕልም ይበናሉ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ይሆናሉ፡፡
6ሣር ወዲያው አድጐ ያብባል ሲመሽ ግን ጠውልጐ ይጠፋል፡፡
7እኛ በቁጣህ ጠፍተናል በመዓትህም ደንግጠናል፡፡
8ኃጢአታችንን በፊትህ፣ የተሰወረ ኃጢአታችንንም በግልጽ በሚታይ ቦታ ታኖራለህ፡፡
9ዘመናችን ሁሉ በቁጣህ ያልፋል ዕድሜያችንም በቅጽበት እንደሚያልፍ እስትንፋስ ነው፡፡
10ዕድሜያችን ሰባ፣ ጤነኞች ከሆንንም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡ እነዚያም ቢሆኑ፣ በመከራና ሐዘን የተሞሉ ናቸው፡፡ ዕድሜያችን ቶሎ ያልቃል፤ እኛም ወዲያው እንነጉዳለን፡፡
11የቁጣህን ኃይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው፡፡
12ጥበበኞች መሆን እንድንችል ዕድሜያችን ምን ያህል መሆኑን አስተምረን፡፡
13ያህዌ ሆይ፣ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል፤ ለባሪያዎችህም ራራላቸው፡፡
14በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ በማለዳ ምሕረትህን አጥግበን፡፡
15መከራ ባየንበት ዘመን መጠን ችግር ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን፡፡
16እኛ ባርያዎችህ ታላቁን ሥራህን፣ ልጆቻችንም ግርማህን እንዲያዩ ፍቀድልን፡፡
17የጌታ አምላካችን ሞገስ እኛ ላይ ይሁን የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ ያድርግልን አዎን ፍሬያማ ያድርግልን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።