1እግዚአብሔር ከተማውን፣ በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ
2ያህዌ የጽዮንን ደጆች ከያዕቆብ መኖሪያዎች ይበልጥ ይወዳል፡፡
3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ ነገሮች ተነግረዋል፡፡ ሴላ
4ከሚያውቁኝ መካከል ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ እነሆ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር ሆነው፣ «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው› ይላሉ፡፡
5ስለ ጽዮን ግን፣ ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት፣ «እነዚህ ሁሉ የተወለዱ እዚያ ነው» ይላሉ፡፡
6ያህዌ ሕዝቦችን ሲመሠርት «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው» ብሎ ይጽፋል፡፡
7ዘማሪዎችና መሣሪያ ተጫዋቾችም፣ «ምንጩ ሁሉ አንቺ ውስጥ ይገኛል» ይላሉ፡፡